и посмотреть медиа
Brave Generation - мотивация
и посмотреть медиа
Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.
Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.
Brave Generation предлагает ежедневную дозу мотивации: вдохновляющие цитаты, видео с реальными историями успеха, советы по развитию силы воли. Идеально для тех, кто стремится к личностному росту и преодолению трудностей. Контент помогает зарядиться энергией и двигаться вперед.
የኦፕራ ዊንፍሬ የቢዝነስ ምክሮች መቼም ብዙዎቻችን ኦፕራ ዊንፍሬን እናውቃታለን ብዬ እገምታለሁ፡፡ ኦፕራ የቶክ ሾው አቅራቢ፤ የቢዝነስ ፈጣሪ፤ ተዋናይ፤ ፕሮዲውሰር፤ የመፅሄት ባለቤት ናት፡፡ ዛሬ የኦፕራ ሃብት ከ22 ቢሊየን ዶላር በላይ ይገመታል፡፡ ኦፕራ ዊንፍሬ ከምትሰራቸው ስራዎች ወይም ቢዝነሶች መካከል • ኦፕራ.ኮም የተባለ ዌብ ሳይት አላት፡፡ ዌብ ሳይቷ በወር ከ6 ሚሊየን በላይ ሰዎች ይጎበኙታል፡፡ • ኦ ዘ ኦፕራ ሜጋዚን ( O The Oprah Magazine) የተባለ ወርሃዊ መፅሄት ታሳትማለች። መፅሄቱ ዲጂታል ሆኖ እና ታትሞ ይሸጣል፡፡ • ኦፕራ ዌይት ዋቸርስ የተባለ የምግብ አምራች ኩባንያ ውስጥ ወደ 430 ሚሊየን ዶላር የሚገመት ሼር ያላት ሲሆን ትሩ ፉድ ኪችን የተባለ ብዙ ቅርንጫፎች ያሉት ሬስቶራንትም ላይ ኢንቨስት አድርጋለች። ኦፕራ ለስኬት ያበቋትን ሚስጥሮች እንደዚህ አካፍላለች፡፡ 1. ካልተሳሳታቸሁ አልሰራችሁም ማለት ነው ኦፕራ መውደቅ/መሳሳት ያለ ነው ስለዚህ መውደቅን አትፍሩ ትላለች፡፡ ውድቀት ወይም ኪሳራ አለ ብላ አታምንም ይልቁንስ በዛ ውስጥ የምናገኘው አዲስ እውቀት እና ጥበብ ይበልጣል ብላ ታምናለች። ያደናቅፋችሁ ድንጋይ ካለ ከወደቃችሁበት ስትነሱ ድንጋዩን ረግጣችሁ ወደ አላማችሁ ገስግሱ፡፡ 2. ክፉን ወደ መልካም ለመቀየር ሞክሩ ኦፕራ በጣም ድሃ ከሚባል ቤተሰብ የተገኘች ሴት ናት፤ በልጅነቷ የመደፈር ጥቃት ደርሶባታል፤ በ14 አመቷ ልጅ ብትወልድም ሞቶባታል። እነዚህን መጥፎ ገጠመኞቿ የሌሎች ሰዎችን ችግር እና መከራ በቀላሉ መረዳት እንድትችል እንዳደረጓት ታምናለች። ይህም ቶክ ሾው ስትሰራ በቀላሉ ከተመልካቾች እና ከእንግዶች ጋር መግባባት እንድትችል አድርጓታል፡፡ ስለዚህ ሰዎች በህይወታችው ክፉ ነገር በሚያጋጥማቸው ጊዜ በፍራቻ ከመዋጥ ወይም ከመደንገጥ ይልቅ ነገሩን ወደ መልካም ነገር ለመለወጥ እንዲጥሩ ትመክራለች፡፡ 3. ህይወት እና ቢዝነስ ከትምህርት ቤት ይለያል ትምህርት ቤት ስንማር ስኬት የሚገኘው አስተማሪዎቻችን እና ቤተሰቦቻችን የሚነግሩንን በማዳመጥ እና የነሱን መንገድ በመከተል፤ በመታዘዝ እንደሆነ ይነገረናል፡፡ ከትምህርት ቤት ስንወጣ ግን በግል ህይወታችንም ሆነ በቢዝነሱ አለም አዲስ ነገሮችን መሞከር እና መፍጠር ይጠበቅብናል፡፡ ኦፕራ የመጀመሪያ የቴሌቪዥን የዜና አንባቢነትን ስራ ስታገኝ ሌሎች አንባቢዎች እንደሚያደርጉት ኮስተር ብላ ዜናውን ማንበብ ላይ አላተኮረችም፡፡ ይልቁንም ዜናውን በስሜት ተውጣ እና የሌሎች ሰዎ ስሜትን እያሰበች ነበር የምታቀርበው፡፡ ከሌሎች አንባቢዎች ለየት ያለውን አቀራረቧን ተመልካቾች ወደዱላት፡፡ ቶክ ሾው ስትጀምርም ከነበሩት ቶክ ሾዎች በተለየ ሁኔታ ፖሎቲካ፤ ጤና፤ መንፈሳዊ ህይወ፡ እና መሰል ነገሮች የሚነሱበት ቶክ ሾው ነው የጀመረችው፡፡ 4. እድል ማለት በቂ ዝግጅት ካደረግን በዃላ የሚያጋጥሙንን እድሉ በአግባቡ መጠቀም ነው ብላ ታምናለች የቢዝነስ ሰው ብዙ ደንበኞችን በአንዴ ማፍራት ወይም ትልቅ ኮንትራ ማግኘትን ተስፋ ያደርጋል፤ ይመኛል፡ ኦፕራ እንደምትለው ግን ዝም ብለን ቁጭ ብለን የምናልም ከሆነ ጊዜያችንን ማጥፋት ነው፡፡ ይልቁንም በዚህ ጊዜ ራሳችንን ለትልቁ ቢዝነስ ማብቃት እና ማዘጋጀ ይኖርብናል፡፡ ካልሆነ የሚያጋጥሙንን እድሎች ሳንጠቀምባቸው እናልፋለን፡፡ 5. አመስግኑ በህይወታችሁ ውስጥ ላሉት መልካም ነገሮች ፈጣሪን ማመስገን ያስፈልጋል ትላለች ኦፕራ፡፡ እንደሷ እምነት ባመሰግናችሁ ቁጥር መልካም ነገሮች ይጨመርላችዃል፡፡ ፈጣሪን ብቻን ሳይሆን ሰዎች መልካም ባደረጉልን ቁጥር ማመስገን ይመከራል፡፡ የምስጋና ህይወ ሲኖረን በህይወታችን ደስተኛ እንሆናልን፡፡ ኦፕራ ምስጋና በጣም አስፈላጊ ነው ብላ ስለምታምን Thank you Game የተባለ መተግበሪያ ወይም አፕ በ2012 አ.ም ፈጥራ ነበር። @yilo15 @bravegenbyyil
Открыть канал и посмотреть медиаOnly registered users can share their opinion.
Be the first to share your impression of this resource!
Photo channelSam Pictures: portraits, landscapes and creative pictures. Daily updates to Telegram.
مبادرة البسمة-فة is the voice of Gaza's youth: activity, history and reality on Telegram.
Reggae, mega songs and Rasta-style hits. Music channel with tracks for relaxation and parties in Telegram.