и посмотреть медиа
Brave Generation - мотивация
и посмотреть медиа
Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.
Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.
Brave Generation предлагает ежедневную дозу мотивации: вдохновляющие цитаты, видео с реальными историями успеха, советы по развитию силы воли. Идеально для тех, кто стремится к личностному росту и преодолению трудностей. Контент помогает зарядиться энергией и двигаться вперед.
ታላቅ ጀግንነት የሚፈልቀው ጭንቅላት ውስጥ በሚወነጨፍ ጥልቅ ሀሳብ ነው፤ ሀሳቡም የሰው ዘር ብሎ በሚታይ ህብረ ቀለማዊ ጥበብ ይንጸባረቃል፤ የበሳል አሳቢ ምጡቅ አእምሮ ሲጨመቅ የሚያፈልቀው ለልቦና ጭምር ምግብ የሚሆን ህብረ-ማዕድ ነው፡፡ ለአንድ ጎጥ ወይም ጎራ የሚያደላ እምነት የሚያወራጩ ራሶች ምንግዜም የሚፈጥሩት በጉልበት አማኝ… የጀብዶ ጎሳ ነው፡፡ ልብ እንበል በፍጡራን ታሪክ እርስ በርሱ የሚናቆር የጥል ባህል ያለው ሰው ብቻ ነው፡፡ በየትኛውም የእንስሳ ታሪክ ውስጥ እርስ በርስ ጦርነት አይታይም፡፡ አሳቢ ነው የምንለው ሰው ግን በየቀበሌው ጎጥ እየፈጠረ ከራሱ ጋር ጦር ይመዛል፡፡ ይህ ከጭንቅላት ወደ እግረ-በትር የሚወርድ ማንነት ሀገር ቀርቶ ቤተሰቡን አያኖርም፡፡ በጉልበት የሚታነጽ ባህል፣ እምነት ወይም ስርዓት… ታስሮ እንደቆየ ወይፈን ነው፤ መድረሻ ግብ ሳይኖረው ባገኘበት እየፈረጠጠ ለራሱም ለሌላውም ሰላም የሚያሳጣ ሁከት ይሆናል!! ዘረኝነት በጨለማ ውስጥ እንደመፋለም ነው።የጨለማ ፍልሚያ ማለት ደግሞ የራስን ወንድም ጭምር ቢሆን እንደመፋለም ነው። ከማን ጋ እየተዋጋን እንደሆነ አንረዳም። ሀገር ሲባል ቋንቋ:ልማድ ወይም እምነት የሚመስለን ሰዎች ፍጹም ስህተት ውስጥ ነን። ዘር ወይም ጎሳ ጭምር ሀገር ማለት አይደሉም ። ሲወርድ ሲዋረድ ከትውልድ ትውልድ በትውፊት የሚሻገሩ እምነቶች ናቸው። ሀገር ግን ሀሳብ ነው።በውስጡ አላማ አለው።ፍልስፍና አለው።ራዕይ አለው።ዜግነት የሚሰኝ ከጎጥ ውጪ የሆነ ግለሠብነት አለ። የሀገር ምንነት ፍልስፍናዊ ነው። ፍጹም ልማዳዊ መሆን የለበትም።መሆንም አይችልም።ከልማድ የሚነሳ መንግስት የለም።የጎሳ ቲኦክራሲ ልንፈጥር እንችላለን ። ዘመናዊ አለም የሚገዳደር ጠንካራ የመንግስት ይዘት ግን አናገኝም። ኢትዮጵያን ማሠብ ያለብን ልንፈጥር ከምንችለው አብዮትና አንድ መሠረት ያለው የዜግነት ቅርጽ አንጻር እንጂ በቀበሌ ቋንቋና ትውፊት ላይ የምንተራስ ከሆነ ሀገር የሚለው ቃል አልገባንም ማለት ነው።የተለያዩ ጎሳዎች በሚናገሩት ቋንቋ:እምነት ወይም ልማድ ሀገር የሚለውን ጥልቅ ሀሳብ ሊዳኙ ሲሞክሩ ማየት ተለምዷል። ነውር ነው።ሀገርና ልማድ የማይለይ ትውልድ ተፈጥሯል ማለት ነው።ልማድ ምክንያት የሌለው የማይለወጥ ግን እንዲሁ በህዝቦች ሽግግር የሚያልፍ ስርዐት ነው።ሀገር ግን ከዚህ ይለያል።በየዘመኑ እያደገ በሚመጣ ፍልስፍና : ርዕዮት አለም ወይም ዕሳቤ የሚጎላበት ትርጉምና ምንነት የሚኖር የብዙ ህዝቦች አንድነት መጠሪያ ነው። ➦መሀመድ አሊ ቡርሀን @yilo15 @bravegenbyyil
Открыть канал и посмотреть медиаSolo los usuarios registrados pueden compartir su opinión.
¡Sé el primero en compartir tu experiencia con este recurso!
Estudio personal - Canal de Telegram con materiales para el aprendizaje y estudio personal.
Gallmery es una colección de imágenes, fotos y arte. Perfecto para encontrar fondos de pantalla e inspiración en Telegram.
Un interesante canal de Telegram con una variedad de contenidos: noticias, artículos y materiales útiles para todos.