и посмотреть медиа
Brave Generation - мотивация
и посмотреть медиа
Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.
Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.
Brave Generation предлагает ежедневную дозу мотивации: вдохновляющие цитаты, видео с реальными историями успеха, советы по развитию силы воли. Идеально для тех, кто стремится к личностному росту и преодолению трудностей. Контент помогает зарядиться энергией и двигаться вперед.
❗#የጋዳፊ_ትንቢታዊ_ንግግር ⤵️ "እኔ ወደየትኛውም ሃገር ተሰድጄ ወይም ጥገኝነት ጠይቄ አልሄድም። የተወለድኩት እዚሁ ነው። የምሞተውም በዚሁ በሃገሬ በሊቢያ ነው። እኔ ወደ ስልጣን ስመጣ ይህ ሃገር ሙሉ በሙሉ በረሃ ነበር። እኔ ግን ሁሉም እፅዋት እንዲበቅልበት አድርጌ ወደ ልምላሜ ቀይሬዋለሁ። ይህችን ሃገር ከራሷ ዜጎች በላይ ማንም አይወዳትም። አሜሪካውያንና አውሮፓውያን እንወዳችኋለን ቢሏችሁ አትመኗቸው። ተጠንቀቁ! እነሱ የሚፈልጉት ሃብታችሁን ነው። እነሱ የሚወዱት የዚህችን ሃገር ነዳጅ እንጅ ህዝቦቿን አይደለም።ዛሬ እናንተ እኔን ትወጉ ዘንድ እያነሳሷችሁና እያገዟችሁ ነው። ነገር ግን እናንተ ከኔ ጎን ቆማችሁ እነሱን ብትዋጉ ብልህነት ነው። ምክንያቱም ምዕራባውያን አሁን እየወጉ ያሉት የወደፊት ተስፋና ራዕያችሁን ነው። ለመላው ሊቢያውያን ማስተላለፍ የምፈልገው አንድ መልእክት አለኝ። ዛሬ ምዕራባውያን እናንተ እኔን ትወጉbዘንድ እያስታጠቋችሁና እየደገፏችሁ ነው። ነገርግን እውነት እላችኋለሁ በኋላ ለዚህ ጥፋት በምትከፍሉት መራራ ዋጋ እጅግ ትጎዳላችሁ። ለእናንተ ለአሜሪካኖችና ለአውሮፓውያንም ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር አለኝ። እናንተ ትገሉኛላችሁ። ነገር ግን እኔ ከሞትኩ በኋላ ለምትጋፈጡት ማቆሚያ የሌለው የሽብር ጦርነት ራሳችሁን አዘጋጁ። እናንተ ከድንቁርናችሁ ሰመመን ከመንቃታችሁ በፊት አሸባሪዎች ጦርነቱን እደጃችሁ ድረስ ያመጡታል።" ጋዳፊ በአሜሪካ ፊትአውራሪነትነና በምዕራባውያን ደጋፊነት በተከፈተባቸው ጦርነት ከመገደላቸውና ሊቢያም አሁን ባለችበት ሁኔታ ከመፈራረሷ በፊት ጋዳፊ የተገደሉት በሃገር ቤት ለዜጎቻቸው፣ በዓለም መድረክም ለተቀረውbዓለም አንባገነን ስለነበሩ ነበር ከተባለና የጋዳፊ መንግስትም ለውድቀት ሃገሪቱም ለመበታተን የበቃችው መንግስታቸው አንባገነን ስለነበረ ብቻ ነው ወደሚለው ከእውነታው ያፈነገጠ መደምደሚያ የምንደርስ ከሆነ "አንባገነን" እና "ዴሞክራሲያዊ" የሚሉት ቃላት ፍች በአተረጓጎም ቦታ ተቀያይረዋል ማለት ነው። እስኪ ጋዳፊ በስልጣን ላይ በነበሩበት ዘመን ሊቢያውያን ያገኙ የነበሩትን የዜግነት ጥቅም አንድ በአንድ እንይና ኮለኔል ጋዳፊ በመጨረሻው ዘመናቸው የተናገሩትን ትንቢታዊ መልዕክት፣ የአሜሪካኖች በሰው ሃገር ጣልቃ የመግባት ውጤት ከሆነችው እና ዛሬ ብትንትኗ ወጥቶ ዜጎቿ ቁራሽ ዳቦ ብርቅ እንዲሆንባቸው ከተደረገችው፣ ለአለም ህዝቦች በተለይም ለመሃከለኛው ምስራቅ ሰላም ስጋት የሆኑ ሽብርተኞች መፈልፈያ ከሆነችው ከዛሬዋ ሊቢያ ጋር እናስተያየውና የራሳችንን ፍርድ እንስጥ… 1 #በጋዳፊ ዘመን በሊቢያ የኤሌትሪክ ሃይል ከክፍያ ነፃ ነበር። የኤሌትሪክ ፍጆታ ቢል ብሎ ነገር አልነበረም። 2 #ማንኛውም ሊቢያዊ የባንክ ብድር ከፈለገ ከወለድ ነፃ በ 0% interest የፈለገውን ገንዘብ መውሰድ ይችል ነበር። 3 #በሊቢያ የመኖርያ ቤት ማግኘት ከሰብዓዊ መብቶች እንደ አንዱ ይቆጠር ነበር። 4 #በሊቢያ ህክምናና ትምህርት በነፃ ይሰጥ ነበር። ከጋዳፊ በፊት 25% የነበረው የተማረ ሰው ሃይል መጠን በእሳቸው ግዜ 83% ደርሶ ነበር። 5 በሊቢያ በግብርና ስራ ላይ መሰማራት የሚፈልግ የእርሻ መሬት፣የግብርና ግብአት ማቀነባበሪያ ቤት፣መሳርያዎችና የተለያየ ቁሳቁስ ከመንግስት በነፃ እንደ ማበረታቻ ይሰጠው ነበር። 6 በሃገር ውስጥ የከፍተኛ ትምህርትና ህክምና ማግኘት ላልቻሉ ዜጎች እነዚህን ወደውጭ ሃገር ሄደው ያሟሉ ዘንድ መንግስት ድጎማ ያደርግ ነበር። 7 ሊቢያውያን አዲስ መኪና ሲገዙ የወጭውን 50% በመንግስት ይደጎሙ ነበር። 8 በሊቢያ የነዳጅ ዋጋ 0.14 ዶላር በሊትር ነበር። 9 ሊቢያ ምንም አይነት የውጭ ብድር ያልነበረባት ሃገር ከመሆኗም በላይ የመንግስት የመጠባበቂያ ካፒታል መጠኗም 150 ቢሊየን ዶላር ነበር። 10 በሊቢያ አዲስ ተመራቂ የሆነ ዜጋ እንደተመረቀ ስራ ካላገኘ በሙያው ቢቀጠር ያገኝ የነበረውን ደሞዝ 50% ያህል ስራ እስኪቀጠር መንግስት ይከፍለው ነበር። 11 ሊቢያ ከነዳጅ ታገኘው ከነበረው ገቢ ግማሽ ያህሉ ወደ እያንዳንዱ ሊቢያዊ የባንክ ሂሳብ ፈሰስ ይደረግ ነበር። 12 በሊቢያ አዲስ ህፃን የምትወልድ ሴት ከመንግስት 5ሺህ ዶላር በሽልማት መልክ ይሰጣት ነበር። 13 በሊቢያ በቁጥር 40 የሚደርስ ሙልሙል ዳቦ ዋጋው የአንድ ዶላር 15 ሳንቲም አካባቢ ነበር። 14 ከሊቢያ ዜጎች 25% ያህሉ የዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ማግኘት ችለዋል። 15 ጋዳፊ በዘመናቸው በዓለም 1ኛ የሆነውንና ሰው ሰራሽ ወንዝ በመባል የሚታወቀውን ፕሮጀክት በመስራትና በእያንዳንዱ በረሃማ ከተሞች ውሃ በየቤቱ እንዲዳረስ ያስቻለ ስራ ሰርተዋል። እንግዲህ ጋዳፊን ለሞት፣ ሃገሪቱን ደግሞ ለማያባራ የእርስ በእርስ ጦርነትና መበታተን የዳረጋት የአንባገነንነት መገለጫ ከላይ የተገለፀው ትሩፋት ከነበረ፣ የሰው ሃገር ሉአላዊነት ምእራባዊያን በፈለጉ ሰዓት እየደፈሩ፣መንግስታትና ህዝቦችን እየከፋፈሉ፣ ህፃናትን ሴቶችንና አረጋውያንን ለማያባራ ሰቆቃ እየዳረጉ ያሉትና ራሳቸውን የዴሞክራሲ መሲሆች አድርገው የሚቆጥሩት አሜሪካውያን እና አውሮፓውያን መገለጫቸው ምን ይሆን…⁉️⁉️ እኛስ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ምን ማድረግ አለብን❓ ሁላችንም ስለእውነት ቆም ብለን እናስብ! 🇪🇹 ፈጣሪ ለኢትዮጵያ ሰላሙን ያምጣላት 🙏🙏 በሳሙኤል ግርማ
Открыть канал и посмотреть медиаТолько зарегистрированные пользователи могут делиться своим мнением.
Станьте первым, кто поделится своим впечатлением об этом ресурсе!
Ассортимент товаров от магазина. Качественные вещи для повседневной жизни.
Канал с прямыми видео трансляциями с камер. Свежие записи онлайн в Telegram.