и посмотреть медиа
Brave Generation - мотивация
и посмотреть медиа
Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.
Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.
Brave Generation предлагает ежедневную дозу мотивации: вдохновляющие цитаты, видео с реальными историями успеха, советы по развитию силы воли. Идеально для тех, кто стремится к личностному росту и преодолению трудностей. Контент помогает зарядиться энергией и двигаться вперед.
ሰለ ድምጻዊ አለማየሁ እሸቴ (በእውቀቱ ስዩም) አለማየሁ እሸቴ በአጸደ- ስጋ አብሮን በነበረበት ጊዜ በተረብም በቁም ነገርም ሳነሳው ቆይቻለሁ ፤ እና የሚከተሉትን ቃላት የምጽፈው “ የሞተ ሰው አንገቱ ረጅም ነው” የሚለውን ልማድ ለመከተል አይደለም :: አለማየሁ እሽቴ, አባቴ ከሚወዳቸው ዘፋኞች እንዱ ነበር:: “ አይዘራፍ እያሉ” “ ከሰው ቤት እንጀራ” የተባሉትን ፤ የልጅነቴን ትዝታ ቀስቃሽ ዘፈኖች ፥ በቅርቡ ዩቲዩብ ላይ ፈልጌ አጣሁዋቸው :: አለማየሁ የፊልም አፍቃሪ እንደነበር ሰምተናል ፤ የወጣትነት ህይወቱም ሲኒማ- መራሽ ነበር፤ የሆነ ጊዜ ላይ አሌክስ ሂልተን ሆቴል ገባ፤ በሚዘናፈለው ጠጉሩ ላይ የቴክሳሰስ ባርኔጣ ገድግዷል ፤ ከወደ ቁርጭምጭሚቴ የሚሰፋ ቦላሌ ለብሷል፤ አግሩን የመመገቢያ ጠረቤዛ ላይ እግሩን አንፈራጦ በመቀመጥ ሲጃራ ማጤ ስ ጀመረ፤ አስተናጋጁ እግሩን እንዲያወርድ ጠየቀው ፤ እምቢ አለ፤ ዘበኛ ተጠርቶ መጣ፤ አሌክስ ፊሻሌ ሽጉጥ አወጣና ተኩሶ የዘበኛውን ኮፍያ አወለቀው ፤ ብዙ ሳይቆይ ፈጥኖ ደራሽና የክቡር ዘበኛ ሂልተን ሆቴልን ከበበው፤ አሌክስ ካዛንቺስ አካባቢ ሲግጥ የቆየውን ፈረሱን በፉጨት ጠራው:: ከዝያ “ እንዳሞራ “ ኮርቻው ላይ ፊጥ ካለ በሁዋላ ጋልቦ አመለጠ፤ ፈረስ የጠራበትን ፉጨቱን ወደ እንጉርጉሮ አሳደገው ፤ በለስ የቀናው ዘፋኝ ሆነ:: አሁን ያወጋሁት እልም ያለ ፈጠራ መሆኑን ተማምነን ወደ ቁምነገሩ እንሂድ:: አሌክስ ከሚጥም ድምጹ ባሻገር ዘናጭ ፤ ከፍተኛ በራስ መተማመን ያለው ሰው ነበር ፤ እጣፈንታ በብዙ ነገር አዳልታለታለች:: ተቸግሮ አልለመነም:: የሆነ ጊዜ ባለስልጣን ሆኖ ያቅሙን ያክል ህዝብ ነድቷል :: አርባ ምናመን አመት በሞቅ ትዳር ቆይቷል፤ ይህንን ያክል ዘመን ባንዲት ወይዘሮ እቅፍ ተወስኖ መቆየት በዘፋኝ አለም ብርቅ ነው ፤ አሌክስ በትዳር የቆየበትን ጊዜ ያክል ኬኔዲ መንገሻ በሕይወት አልቆየም:: ሙሉቀን መለሰ የሚያደንቀው ብቸኛ ዘፋኝ የጋሽ እሸቴን ልጅ ነው:: አለማየሁ በዘመናችን ካሉ ዘፋኞች የጎሳየ ተስፋየ አድናቂ መሆኑን ነግሮኛል:: “ የወይን አረጊቱ” “፥ አዲሳበባ ቤቴ’ ፥ “ አምባሰል “ እንደ ጥንቱ መስሎኝ””፥ ልተለየሽኝም “ ታሪክሽ ተጽፏ ል” የሚሉት ዘፈኖቹ ዘመን አልሻራቸውም፤ በጸጋየ ወይን ገብረመድህን( ደብተራው) የተደረሰው “ ያ ጥቁር ግስላ” የተሰኘው ዘፈኑ ራሱን የቻለ አቢዮት ነው ማለት ይቻላል :: “ የአስር ሳንቲም ቆሎ ፤ ቁርጥም አደርግና “ እሚለው ዘፈኑ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከየት ወዴት እንደ ሄደ ያመላክታል ፤ ለካ አስር ሳንቲም ሙዝየም ከመግባቱ በፊት ይሄን ያህል ሙያ ነበረው :: “ ካጣን ምናባቱ እንብላ ሽንብራ የሰው እጅን ብቻ እንዳናይ አደራ “ የሚለውን ዘፈንስ እንዴት ይረሳል? በአሌክስ የጉርምስና ዘመን፥ ያጣ የነጣው ድሃ ሽምብራ ተመጋቢ ነበር፤ አንዳንዴ ዜጎች የድሮውን ቢናፍቁ ምክንያት አላቸው :: አሌክስ የተረፈው ሀብታም ልጅ ነበር ፤ በጉርምስና ዘመኑ አንዴ ለመሰደድ የወሰነው እንጀራ ለማደን ሳይሆን የሆሊውድ አክተር የመሆን ምኞቱን ለማርካት ነበር :: ቢሆንም ስለ ድህነት አብዝቶ በመዝፈን ድሀ- አደግ ዘፋኞችን ሳይቀር ይቦንሳል :: በተለይ ኮለኔል ግርማ ሐይሌ ከተባለ ደራሲ የተቀበላቸው እንጉርጉሮዎች ከምሾ በላይ ሆድ የሚያስብሱ ናቸው :: እዚህ ላይ “ ስቀሽ አታስቂኝ “ የሚለው ፒያኖውን የሚያስለቅስበት ዜማው ትዝ ይለኛል፤ የዘፈኑ ባለታሪክ የሙት ልጅ የሆነች ድሃ ናት:: ኑሮን ለማሸነፍ “ትፍጨረጨራለች” ፤ በመከራዋ ላይም ትስቃለች :: ይህ በእንዲህ እያለ ወንድምየው ጣልቃ ገብቶ “ ስቀሽ አታስቂኝ “ ይላታል ፤ ““ ትፍጨረጨርያለሽ ወጉ አይቀር ብለሽ “ እያለ ያዳክማታል :: ጭራሽ “ ውሃ ጉድጉዋድ ግቢ የምየ ልጅ ባክሽ ” እያለ ይጎተጉታታል ፤ የሰው ልጅ ሁኔታ በጠቅላላው፤ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ሁኔታ ተስፋ አስቆርጦኝ ያውቃል ፤ “ስቀሽ አታስቂኝ”ን ስሰማ ግን እኔን ብሎ ተስፋ ቆራጭ እላለሁ፡: እንደዚህ ተስፋን ከጎድንና ከዳቢቱ እሚቆርጥ ዘፈን ገጥሞኝ አያውቅም :: ሰው ማለቂያ በሌለው ውድቀት መሀል እንኳን እየኖረ ተስፋና መጽናኛን የሚያማትር ፍጡር ነው ፤ ከአለማየሁ እሸቴ “ ስቀሽ አታስቂኝ “ ይልቅ የ አለማየሁ ሂርጶ” አታቀርቅሪ ቀን ያልፋል “ የሚለውን ዘፈን ይበልጥ የገነነው ለዚህ ይሆን ? @yilo15 @bravegenbyyil
Открыть канал и посмотреть медиаТолько зарегистрированные пользователи могут делиться своим мнением.
Станьте первым, кто поделится своим впечатлением об этом ресурсе!
Канал D предлагает подборку интересных материалов: от новостей до полезных советов для повседневной жизни.
Траур по советникам из 'Игры престолов'. Юмористические истории и намеки на судьбы ярких умов семи королевств.
Центр для поклонников оружия, рыбалки и активного отдыха. Новости, снаряжение и всё необходимое для хобби.