Logo
TGCATALOG
Каталог Подборки Блог
Brave Generation - мотивация

Brave Generation - мотивация

Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.

Нет оценок
197
10.09.2026
197
10.09.2026
Нет оценок
197
10.09.2026
Безопасный переход через бот
О канале

Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.

Подписчиков 95
Тематика Другое
Язык Русский
Ссылка t.me/bravegenbyyil
Описание

Brave Generation предлагает ежедневную дозу мотивации: вдохновляющие цитаты, видео с реальными историями успеха, советы по развитию силы воли. Идеально для тех, кто стремится к личностному росту и преодолению трудностей. Контент помогает зарядиться энергией и двигаться вперед.

Последние посты

Brave Generation - мотивация
Brave Generation - мотивация
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
ፈጣሪ ርቦት ✍️ ገጣሚ እና ባለቅኔ ኤፍሬም ስዩም እግዚአብሔር በመንገድ ላይ...በመንገድ ላይ ፈጣሪን ሲመላለስ ከሩቅ አስተዋልኩት። ከስቶ ነበር። ፊቱ ገርጥቷል። ቁመተ ዘልአለም.. ፀጉሩ እንደጥጥ ስስ እና ነጭ ነበር፡፡ አንጀቱ ተጣብቋል። ባህር መሳይ ውሃ ቀለም ዓይኑ፡ ነዶ ያለቀ የከሰል ፍም መስሏል። ረጅም መንገድ ተጉዞ ነበር፡፡ የፈለገውን ግን አላገኘም። በእጁ እና በቃሉ በፈጠራት ምድር ላይ እንደ መፃተኛ ነበረ። በምድር ላይ በሚመለከተው ሁሉ ሃዘንተኛ ይመስላል። በሰዎች መሃል ሲመላለስ ሰዎችን ይወቃቸው እንጂ ሰዎች እሱን ልብ አላሉትም ነበር። ከኋላው ተከተልኩት፣ ከኋላው እጅግ በጣም እርቄ... ከኋላው እየተከተልኩት የማስተውለው የሰውን ልጅ አልነበረም፡፡ ፈጣሪን ነበር። የሰው ልጆች ሁሉ ፈጣሪ... የክርስቲያን እና የሙስሊሙን፤ የሴቶች እና የወንዶችን፤ የከሃዲያን እና የአማኞችን፤ የነጭ እና የጥቁሮችን፤ የእዚህን እና የዚያን አለም እሱን ነበረ።ከኋላው እየተከተልኩ፣ በገባበት እየገባሁ፣ የተጓዘባቸው ቦታዎችን እና ስፍራዎችን ልብ እያልኩ፣ ጸጉሩ የነጣውን፣ፊቱ የገረጣውን፣ አይኑ ጨረር እንባ የሚረጨውን፣ ከኋላ ሁኜ ስለምን ፊቱ ገረጣ? ስለምንስ ከዓይኑ የጨረር እንባዎች ይወድቃሉ? እንዴትስ የደከመው መሰለ? እያልኩ ተከተልኩት። ከኋላው ነበርኩ ወደ ቤተ-መቅደስ ገባ፡፡ ካህኑ ፊቱን መደ ህዝቡ መልሶ ቆሞ ነበር። ህዝቡን እየባረከ፡፡ እግዚኣብሔር በህዝቡና በካህኑ ፊት ቆመ... ከዓይኑ ጥግ ይወርድ የነበረው ጨረራማ እንባ ቤተ- መቅደሱን ከደነው፡፡ እሳት መሳይ በሆነ በእግዚአብሔርም እንባ መካከል ቆመው የነበሩ ካህናት እና ምእመናን በእንባው መሃል መቆማቸውን ልብ አላሉም፡፡ ፊቱን እዙሮ ከመቅደሱ ወጣ፡፡ ማለዳ ፀሃይ ልትወጣ ስትል የምትመስለውን ይመስል የነበረ ደረቱ ከቀደመው ይልቅ ገረጣ፡፡ እርሃብ ያሽነፈውን ሰው መሰለ። ደም ግባት በፊቱ አልነበረም፡፡ እናቱ የሞተችበት ልጅን የሚመስል ሃዘን በፊቱ ላይ ነበረ። መንገዱን ቀጠለ፡፡ ቀድሞ ከወጣበት ቤተ-መቅደስ አለፍ ብሎ ከሚገኝ "መስጊድ" ዘለቀ። ሰላቱን በሚያሰግደው “ኢማም” እና “በጀማው” መካከል ፈጣሪ ቆመ፡፡ ጥቂት ቆይቶ ተመልሶ ወጣ በመቅደሱ እንደነበረው በዚህም ገፅታው እንደዚያው ነበር፡፡ ፍፁም ሃዘንተኛ፡፡ ከቀደመው ይልቅ አሁንም ሃዘን በፊቱ ላይ ነበር፡፡ ከኋላው መከተሌን ቀጠልኩ፤ እርቄ ከኋላው... ከተወሰነ የደከመ ጉዞ በኋላ ወደ አንድ ሰፊ ምኩራብ ዘለቀ፡፡ የኢየሱሳዊያን ጉባዔ በዛ ነበር፡፡ ከመሃከላቸው ቆመ እዛው በቆመበት የሚያስደነግጥ ሁኔታ ሆነ፡፡ ማለቂያ የለሽ ቁመናው ዛለ፣ እግሩ ተብረከረከ፤ ወዲያው በጉልበቱ ታጥፎ በምኩራቡ ላይ ተንበረከከ፡፡ ሁኔታው በጦር ሜዳ ስም የለሽ በሆነ ወታደር ጉልበቱን በጦር ተመቶ የወደቀን ስመ-ጥር ጀግናን ይመስላል፡፡ ከወደቀበት ፈጥኖ ተነስቶ ወደ መውጫው አመራ....አረማመዱን ከርቀት አስተዋልኩት። ዘላለም የለሽ እግሩ "ያነክስ" ነበር። እዎን ከዚያ ሲወጣ ያነክስ ነበር፡፡ ከዓይኖቹ ይረጩ የነበሩት የሃዘን ጨረሮች እንደወንዝ ነበሩ፡፡ እያነከሰ ወደ ቤተ መንግስት አመራ፡፡ እየተንፏቀቀ ተመልሶ ወጣ። እየተንፏቀቀ ርዕሰ ብሄሩ መኖሪያ ወጣ፡፡ ከአንደበቱም ቃል ይስማም ነበር። "በዚህ ሁሉ ነገር ባዶ ነው!!" በማለት እያቃሰተ አዘገመ። በመንፏቀቁ የተጎዳ ጉልበቱ የቀለጠ ብዙ እሳት የጠገበ የተፈተነ ወርቅን ይመስል ነበር፡፡ ተከተልኩት። ከጥቂት የደከመ እርምጃ በኋላ ጎዳና ያደከማቸው መንገደኞች ሁሉ ሊመርጡት ከሚችሉት ረጅም ዋርካ ስር ከሚገኝ አለት ላይ አረፍ አለ። እዚህ አለት ስር የመቅደስ ደረት፣ የመስጊድ አንጀት ፣ በር የሚዘጋባቸው ቤት የለሽ ህፃናት፤ ወንዶች እና ሴቶች ቀን ቀን ያለእራፊ ጨርቅ የሚተኙበት እና የሚጠለሉበት ስፍራ ነው፡፡ እሱንም የቤተመንግስቱን ህግ እናስከብራለን የሚሉ ጭፍራዎች ካላሳደዱአቸው ነው፡፡ በዚያ ፈጣሪ ተቀመጠ፡፡ እውነትም ገፁ "እህል ከቀመሰ ዘመናት ያለፉትን ጎልማሳ" መስሏል፡፡ ስለምን መስሏል ? ሆኗል እንጂ፡፡ ርቄ ከኋላው እከተለው የነበርኩ በውስጤ ጥያቄ እየተመላለሰ ወደ ተቀመጠበት ተጠጋሁ ፈጣሪ እንዴት ሊራብ ይችላል? ሲርበው ምን ሊመገብ ይችላል? ሰማይ እና ምድርን በጣቱ የፈጠረ እሱ እንዴት ሊራብ ይችላል?? በባህር እና በምድር ያሉትን ፍጥረታትን የሰራ እሱ ምን ሊመገብ ይችላል??? እርሃብተኛ መስሎ በህዝቡ እና በአምልኮ ስፍራዎቻቸው የተመላለሰ ለእሱ ምን አይነት ምግብ ሊሰራ ይችላል? ከዋርካው ስር ከአለቱ ላይ የተቀመጠ ፈጣሪ ምን ቢርበው ይሆን ደረቱ የገረጣ? ፊቱ የጠወለገ? አንጀቱ የታጠፈ አይኑ የሰረጎደ መስሎ የሚታየው??? ይህንን በልቤ እየጠየቅሁ ርቄ ከጎኑ ተቀመጥኩ... አይኖቹን ወደ እኔ መለሰ፡ እኔ በውስጤ ጠፋሁ:: በውጪም አልነበርኩም። ገብቶ ካዘነባቸው ስፍራዎች በአንዱ ነበርኩና። ከዓይኑ ጥግ ወርዶ በጨረር ፍም ከሞላው ስፍራ። ከአንደበቱ "ቃል" ወጣ... "ስለምን ትከተለኛለህ"? አለኝ... "ለምድሪቱ እንግዳ ስለመሰልከኝ" አልኩ በፍርሃት በቸርነቱ በተለገሰችኝ ድፍረት። "አዎን እንግዳ ነኝ" ማረፊያ ያጣሁ ርሃብተኛ፡ ቁራሽ እቀምሰው ያጣሁ ምፅዋተኛ ነኝ... በፈጠርኩት ምድር ላይ እንግዳ ነኝ፡፡ እንዲህ አይነት ህይወትና መሬት በእጄ አልተፈጠረም፡፡ በአንደበቴም አልጸናም፡፡ ሁሉንም ዞሬ ጎበኘው። አለምን ሁሉ ቃኘሁ። ይህ አለም በእናንተ እንጂ በእኔ የተፈጠረ አይደለም። እኔ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ፈጠርኩ፡፡ እናንተ ግን የማያስፈልጋችሁን ሁሉ መረጣችሁ። የመረጣችሁት እኔ የሰራሁት አይደለም፡ እናንተ የፈጠራችሁት እንጂ። እናንተ በፈጠራችሁት ግን እኔ "ርሃብተኛ" ሆንኩ። በድጋሚ ጠየቅኩ፡ ልቤ በውስጤ እየደነገጠ አይኑን እየሸሸሁ "አንተ የሚታይ እና የማይታየውን አለም የፈጠርክ ነህ። ሁሉ በእጅህ... ሁሉ በደጅህ ነው። ምግብን የፈጠርክ አንተ እንደምን ልትራብ ትችላለህ? " መልሼ ጠየቅሁ። ፈጥኖ መለሰልኝ፡፡ ጆሮዎቼ እንጂ አይኖቼ ከፊቱ ሸሽተው ነበር። @bravegenbyyil
Brave Generation - мотивация
Динамика подписчиков
+0.0% за 30 дней
Текущие
95
Месяц назад
95
Средний рост
+0 / день
Обновлено
21 час назад

Отзывы о канале Brave Generation - мотивация

Авторизуйтесь, чтобы оставить отзыв

Только зарегистрированные пользователи могут делиться своим мнением.

Пока нет отзывов

Станьте первым, кто поделится своим впечатлением об этом ресурсе!

Похожие ресурсы

wildlife & landscape photography

Канал

Публикации новых книг и статей из Fifth Estate Anarchist Libraries. Актуальный контент по анархизму и альтернативным взглядам.

Канал

Официальный канал Bijan Nemoy: музыка, видео, тексты и фото.

Канал
Переход на светлую тему
Главная Каталог Подборки Блог Вход