Logo
TGCATALOG
Каталог Подборки Блог
Brave Generation - мотивация

Brave Generation - мотивация

Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.

Нет оценок
56
09.09.2026
56
09.09.2026
Нет оценок
56
09.09.2026
Безопасный переход через бот
О канале

Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.

Подписчиков 95
Тематика Другое
Язык Русский
Ссылка t.me/bravegenbyyil
Описание

Brave Generation предлагает ежедневную дозу мотивации: вдохновляющие цитаты, видео с реальными историями успеха, советы по развитию силы воли. Идеально для тех, кто стремится к личностному росту и преодолению трудностей. Контент помогает зарядиться энергией и двигаться вперед.

Последние посты

Brave Generation - мотивация
Brave Generation - мотивация
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
የኦፕራ ዊንፍሬ የቢዝነስ ምክሮች መቼም ብዙዎቻችን ኦፕራ ዊንፍሬን እናውቃታለን ብዬ እገምታለሁ፡፡ ኦፕራ የቶክ ሾው አቅራቢ፤ የቢዝነስ ፈጣሪ፤ ተዋናይ፤ ፕሮዲውሰር፤ የመፅሄት ባለቤት ናት፡፡ ዛሬ የኦፕራ ሃብት ከ22 ቢሊየን ዶላር በላይ ይገመታል፡፡ ኦፕራ ዊንፍሬ ከምትሰራቸው ስራዎች ወይም ቢዝነሶች መካከል • ኦፕራ.ኮም የተባለ ዌብ ሳይት አላት፡፡ ዌብ ሳይቷ በወር ከ6 ሚሊየን በላይ ሰዎች ይጎበኙታል፡፡ • ኦ ዘ ኦፕራ ሜጋዚን ( O The Oprah Magazine) የተባለ ወርሃዊ መፅሄት ታሳትማለች። መፅሄቱ ዲጂታል ሆኖ እና ታትሞ ይሸጣል፡፡ • ኦፕራ ዌይት ዋቸርስ የተባለ የምግብ አምራች ኩባንያ ውስጥ ወደ 430 ሚሊየን ዶላር የሚገመት ሼር ያላት ሲሆን ትሩ ፉድ ኪችን የተባለ ብዙ ቅርንጫፎች ያሉት ሬስቶራንትም ላይ ኢንቨስት አድርጋለች። ኦፕራ ለስኬት ያበቋትን ሚስጥሮች እንደዚህ አካፍላለች፡፡ 1. ካልተሳሳታቸሁ አልሰራችሁም ማለት ነው ኦፕራ መውደቅ/መሳሳት ያለ ነው ስለዚህ መውደቅን አትፍሩ ትላለች፡፡ ውድቀት ወይም ኪሳራ አለ ብላ አታምንም ይልቁንስ በዛ ውስጥ የምናገኘው አዲስ እውቀት እና ጥበብ ይበልጣል ብላ ታምናለች። ያደናቅፋችሁ ድንጋይ ካለ ከወደቃችሁበት ስትነሱ ድንጋዩን ረግጣችሁ ወደ አላማችሁ ገስግሱ፡፡ 2. ክፉን ወደ መልካም ለመቀየር ሞክሩ ኦፕራ በጣም ድሃ ከሚባል ቤተሰብ የተገኘች ሴት ናት፤ በልጅነቷ የመደፈር ጥቃት ደርሶባታል፤ በ14 አመቷ ልጅ ብትወልድም ሞቶባታል። እነዚህን መጥፎ ገጠመኞቿ የሌሎች ሰዎችን ችግር እና መከራ በቀላሉ መረዳት እንድትችል እንዳደረጓት ታምናለች። ይህም ቶክ ሾው ስትሰራ በቀላሉ ከተመልካቾች እና ከእንግዶች ጋር መግባባት እንድትችል አድርጓታል፡፡ ስለዚህ ሰዎች በህይወታችው ክፉ ነገር በሚያጋጥማቸው ጊዜ በፍራቻ ከመዋጥ ወይም ከመደንገጥ ይልቅ ነገሩን ወደ መልካም ነገር ለመለወጥ እንዲጥሩ ትመክራለች፡፡ 3. ህይወት እና ቢዝነስ ከትምህርት ቤት ይለያል ትምህርት ቤት ስንማር ስኬት የሚገኘው አስተማሪዎቻችን እና ቤተሰቦቻችን የሚነግሩንን በማዳመጥ እና የነሱን መንገድ በመከተል፤ በመታዘዝ እንደሆነ ይነገረናል፡፡ ከትምህርት ቤት ስንወጣ ግን በግል ህይወታችንም ሆነ በቢዝነሱ አለም አዲስ ነገሮችን መሞከር እና መፍጠር ይጠበቅብናል፡፡ ኦፕራ የመጀመሪያ የቴሌቪዥን የዜና አንባቢነትን ስራ ስታገኝ ሌሎች አንባቢዎች እንደሚያደርጉት ኮስተር ብላ ዜናውን ማንበብ ላይ አላተኮረችም፡፡ ይልቁንም ዜናውን በስሜት ተውጣ እና የሌሎች ሰዎ ስሜትን እያሰበች ነበር የምታቀርበው፡፡ ከሌሎች አንባቢዎች ለየት ያለውን አቀራረቧን ተመልካቾች ወደዱላት፡፡ ቶክ ሾው ስትጀምርም ከነበሩት ቶክ ሾዎች በተለየ ሁኔታ ፖሎቲካ፤ ጤና፤ መንፈሳዊ ህይወ፡ እና መሰል ነገሮች የሚነሱበት ቶክ ሾው ነው የጀመረችው፡፡ 4. እድል ማለት በቂ ዝግጅት ካደረግን በዃላ የሚያጋጥሙንን እድሉ በአግባቡ መጠቀም ነው ብላ ታምናለች የቢዝነስ ሰው ብዙ ደንበኞችን በአንዴ ማፍራት ወይም ትልቅ ኮንትራ ማግኘትን ተስፋ ያደርጋል፤ ይመኛል፡ ኦፕራ እንደምትለው ግን ዝም ብለን ቁጭ ብለን የምናልም ከሆነ ጊዜያችንን ማጥፋት ነው፡፡ ይልቁንም በዚህ ጊዜ ራሳችንን ለትልቁ ቢዝነስ ማብቃት እና ማዘጋጀ ይኖርብናል፡፡ ካልሆነ የሚያጋጥሙንን እድሎች ሳንጠቀምባቸው እናልፋለን፡፡ 5. አመስግኑ በህይወታችሁ ውስጥ ላሉት መልካም ነገሮች ፈጣሪን ማመስገን ያስፈልጋል ትላለች ኦፕራ፡፡ እንደሷ እምነት ባመሰግናችሁ ቁጥር መልካም ነገሮች ይጨመርላችዃል፡፡ ፈጣሪን ብቻን ሳይሆን ሰዎች መልካም ባደረጉልን ቁጥር ማመስገን ይመከራል፡፡ የምስጋና ህይወ ሲኖረን በህይወታችን ደስተኛ እንሆናልን፡፡ ኦፕራ ምስጋና በጣም አስፈላጊ ነው ብላ ስለምታምን Thank you Game የተባለ መተግበሪያ ወይም አፕ በ2012 አ.ም ፈጥራ ነበር። @yilo15 @bravegenbyyil
Brave Generation - мотивация
Brave Generation - мотивация
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
"ሰው የተፈጠረለትን አላማ መረዳት ሲሳነው ደስታና እርካታ ይርቀዋል፡፡" አርስቶትል በህልውናችን ውስጥ ያለምክንያት የሚፈጠር ነገር የለም፡፡ ከእያንዳንዱ ፍጥረት በስተጀርባ አላማ አለ፡፡ ህይወትም ሆነ ሞት የተፈጠሩት በምክንያት ነው፡፡ ተፈጥሮ ማንኛውንም ነገር በከንቱ አትፈጥርም ሰዎችም እንዲሁ የራሳቸው ተፈጥሯዊ አላማ፣ ግብና አቅጣጫ አላቸው፡፡ የአላማቸውና የተልእኳቸው ስኬት ውበት፣ እርካታና ደስታን ይፈጥራል፡፡ አምላክ ሰውን የፈጠረው በምክንያት፣ በአላማ ነው፡፡ ሰው የተፈጠረለትን አላማ መረዳት ሲሳነው ደስታና እርካታ ይርቀዋል፡፡ በአንጻሩ የተፈጠረበትን ምክንያት ተገንዝቦ ተልእኮውን ማሳካት ሲችል የአእምሮ ሰላምና የመንፈስ እርካታን ያገኛል፡፡ በብዙሀኑ ዘንድ ( Self - Realizationism) በመባል ፣ የሚጠራው የአርስቶትል የስነ ምግባር ፍልስፍና መልካም ህይወት ወይም ደስተኝነት ባህሪን፣ ሰብእናንና እምቅ ሀይልን ሙሉ ለሙሉ ጥቅም ላይ ከማዋል ይመነጫል የሚለውን እሳቤ መሰረት ያደረገ ነው፡፡ አንድ ህጻን እንደተወለደ ሰው አይባልም ሰው የመሆን እምቅ ሀይል ያለው ግን ሰው ለመባል ያልደረሰ ፍጡር ነው፡፡ እውነተኛ ሰው ለመሆን እምቅ ሀይሉ እውን ሆኖ መታየት አለበት፡፡ አንድ ሰው ከቤትሆቨን ያልተናነሰ ዜማዊ ተሰጥኦ ተችሮት ተሰጥኦውን ማወቅ ከተሳነው ወይም እያወቀ መጠቀም ካቃተው ከቶውኑ አርቲስት ሊሰኝ አይችልም፡፡ ታላቅ አርቲስት ለመሆን የሚያበቃ እምቅ ሀይል ቢኖረውም ሀይሉንና ተሰጥኦውን ጥቅም ላይ እስካላዋለው ድረስ የአርቲስትነት ተሰጥኦ ስላለው ብቻ አርቲስት አይባልም፡፡ እንደ አርስቶትል እሳቤ የሰው ልጅ ተቀዳሚ አላማ ተፈጥሮውና ተሰጥኦው እስከፈቀደለት አጥናፍ ተለጥጦ እምቅ ሀይሉን እውን ማድረግና ምሉእነትን መጎናጸፍ ነው፡፡ ይህን ማድረግ የቻለ ሰው ተልእኮውን ከመወጣት ስሜት የሚመነጭ የተሟላ እርካታና ደስታ ያገኛል፡፡ አንድ የአበባ ዘር ሊያብብ፣ ሊፈካና ሊያፈራ የሚችለው የእድገት ኡደቱን አጠናቆ ውበቱንና ሙሉነቱን አሟልቶ ሲገኝ ብቻ ነው፡፡ ሰው በርካታ ውስብስብ ባህሪያትን ይዞ ቢፈጠርም ተልእኮውን መወጣት ከቻለ ስኬታማ የሆነ ውብ፣ ደስተኛና ምሉእ ፍጡር ይሆናል፡፡ From..... የስብዕና ልህቀት @bravegenbyyil
Brave Generation - мотивация
Brave Generation - мотивация
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
🔆ለራሳችሁ ዋጋ ስጡ! 🌗አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች እኛን በምን መልኩ እንደሚያስተናግዱን (Treat እንደሚያደርጉን) የምናስተምራቸውና የምንፈቅድላቸው እኛው ራሳችን ነን፡፡ 🔆ራሳችንን ከናቅን ሰዎች እኛን ይንቁናል፣ ራሳችንን ስናከብር ደግሞ ያከብሩናል፡፡ ራሳችንን ርካሽ አድርገን ካሰብንና ልክ የትም መሄጃ እንደሌለው አይነት ሰው ሆነን ራሳችንን ካቀረብን ሰዎች እንደ ተራና የትም መሄጃ እንደሌለው ሰው ያስተናግዱናል፣ ለራሳችን ዋጋ ከሰጠን ደግሞ ዋጋ ይሰጡናል፡፡ 🌗ሰዎች በምን መልኩ እየቀረቧችሁና እያስተናገዷችሁ እንዳሉ ተመልከቱትና ምናልባት በዚያ መልክ እንዲቀርቧችሁና እንዲያስተናግዷችሁ የፈቀዳችሁት እናንተው የመሆናችሁን ጉዳይም በዚያው ለመቃኘት ሞክሩ፡፡ 🔆እናንተ ሳትፈቅዱላቸው ሰዎች ሊንቋችሁና በወረደ መልኩ ሊያስተናግዷችሁ አይችሉም፡፡ ከእናንተ ፈቃድ ውጪ በዚያ መልክ እንዳይቀርቧችሁ ማድረግ ባትችሉም ሁኔታው ልክ በማስያዝ ድርጊታቸው የመጀመሪያና የመጨረሻ እንዲሆን የማድረግ መብቱም ሆነ አቅሙ አላችም፡፡ ፈጣሪ ከሰጣችሁ “ሰውነት” በታች አትኑሩ! ✍ዶ/ር እዮብ ማሞ @yilo15 @bravegenbyyil
Brave Generation - мотивация
Brave Generation - мотивация
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
🔆በህይወት እስካለህ ልትሳሳት ፣ ልትወድቅ ትቸላለህ ፣ ሰዎች ላይቀበሉህ ይችላሉ ፣ ወይም ሀሳብህን ላይረዱህ ፣ ቦታ ላይሰጡህ ይችላሉ ፣ በእጅህ ላይ ያለው ሙሉ በሙሉ አመድ ሆኖ ልታገኘው ትችላለህ ፣ ሰዎች ሊጠሉህ ፣ ሊያሙህ ፣ ወይ ስም ሊያወጡልህ ፣ አሊያም ሊስቁብህ ፣ ይችላሉ ። 🔆በህይወት ውስጥ ትልቁ ስህተት ለሁሉም ሰው ትክክለኛ ሆኖ ለመታየት መሞከር ነው ። መልካም ብትሆን ክፉዎች ይጠሉሀል። አዋቂ ብትሆን አላዋቂዎች ባዶነታቸውን ስለምትገልጥባቸው አብዝተው ይፀየፉሀል። ብርሃናዊ ራዕይ ቢኖርህ የጨለምተኞችን ጨለማ ስለምታሳይ መኖርህ ያንገበግባቸዋል ። ነፃ አውጭ ብትሆን ጨቋኞች ያሳድዱሀል። 🔆ምናለፋህ በአለም ስትኖር በሙሉ ድምፅ ልትወደድም፣ ልትጠላም አትችልም። ስለዚህ በደረስክበት ሁሉ ልክ እንደ ውሃ ቅርፅህን አትቀያይር ! ከምንም በላይ በፈጣሪህ ፊት ትክክል ሁን!" አንድ ነገር ልንገራችሁ! 💜በህይወታችሁ ማንንም አትውቀሱ ጥሩ ሰዎች ደስታን ይሰጡዃቿል መጥፎ ሰዎች ልምድ ይሆኑዃችኋል ክፉ ሰዎች ማስጠንቀቂያ ይሆኑዃችኋል ምርጥ ሰዎች ትዝታ ይሆኑዃችኋል። ✍ ጋሽ ስብሃት ገ/እግዚአብሄር @yilo15 @bravegenbyyil
Brave Generation - мотивация
Brave Generation - мотивация
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
#ማምሻ_ስድስት ከመካከላችን ለኔም ላንቺም ያልተቻለን ነገር ያለ ይመስለኛል። ምን ብለሽ ግን አትጠይቂኝ ለኔም፤ላንቺም መልስ የለኝም። ✍ይል @yilo15 @bravegenbyyil
Brave Generation - мотивация
Brave Generation - мотивация
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
#በራ_የመስቀል_ደመራ የአደይ ችቦ እየፋመ እየጋመ ኢዮሃ እያስገመገመ እየተመመ የመስቀል ደመራ በራ። በራ የአዲስ ዘመን ችቦ በመስከረም ላብል እብቦ ከዋከብቱን ፈነጠቀ ርችቱን አንጸባረቀ ተኳለ አዲስ ደመቀ መለኩን በቀለም እዝርእት በጥበብ አጥለቀለቀ ሸለቆው ተንቆጠቆጠ፥ ተራራው አሸበረቀ ኢዮሃ ኢዮሃ አበባዬ! ምድር ሕይወት አፈለቀ። ነጋ፥ የእዲስ ዘመን ችቦ ፈካ፥ ፀደይ አርብቦ ሌሊቱ እንደጎሕ ቀደደ፥ ጨለማው እንደ ቀን ጠራ እንደውቅያኖስ ዕፅዋት እንደጠፈር ኮከብ ደራ ምድር ሥጋጃ ለበሰ፥ የጌጥ አልባሳት ተቀባ ሰማይ በእልልታ እስተጋባ እዮሃ መስከረም ጠባ። ነጋ የአዲስ ዘመን ችቦ፥ ምድር ሕይወት አፈለቀች የምሥራች እዝርእቷን፥ እዲስ ቡቃያ ወለደች የአደይ አበባን ለገሠች ለአዲለ ዘመን አዲስ ብርሃን፥ አዲስ መስከረም ገበየች። ነጋ፥ የአዲስ ዘመን ችቦ ፈካ፡ ፀደይ እረብቦ በራ፥ የመስቀል ደመራ። መስከረም - ፲፱፻፳፫ - መስቀል አደባባይ 🔘ፀጋዬ ገብረመድህንን🔘 @yilo15 @bravegenbyyil
Brave Generation - мотивация
Brave Generation - мотивация
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
#ማምሻ_ዓምስት ከስኬታማ ወንድ ጀርባ አንድ ጠንካራ ሴት አለች… ከአንድ ስለፍቅር ከሚሰብክ ስኬታማ እብድ ጀርባም ጠንካራ ሴት አለች ጤና ማጣቱ አይደለም እሱን እብድ ያስባለዉ ወይም የአይምሮ መቃወሱ አይደለም፡፡ የእሷ በእሱ ውስጥ ተደብቆ መኖር እንጂ፡፡ እሷም ጠንካራ የሆነቺዉ በእሱ ነብስ ዉስጥ መኖር ስትጀምር ነዉ፡፡ በምናቡ አንግሷታል፣በገዛ ነፍሱ ላይ አዛዥ አድርጎ ሾሟታል፡፡ ሲያሻት ደስትኛ ሲላት ሀዘንተኛ ታረገዋለች፡፡ ሳቁ ሲያምራት ክትክት አድርጋ ስታስቀዉ፣ ለቅሶዉ ሲናፍቃት ደሞ ስቅስቅ አድርጋ ታስለቅሰዋለች፡፡ ለሱ ግን ሕይወት ክትክት ብሎ ማልቀስ ስቅስቅ ብሎ መሳቅ ሆኖበታል ✍ይል @yilo15 @bravegenbyyil
Brave Generation - мотивация
Brave Generation - мотивация
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
You will never find another me. Not sure that's a good thing or a bad thing, but it's the truth.😇 @Quotes_TM 🔥
Brave Generation - мотивация
Brave Generation - мотивация
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
እናቷን ጨረቃ . ©ሲራክ ወንድሙ Each day provides its own gifts. ( የአሜሪካውያን አባባል ) አንዳንድ ንጋቶች ነብሴን በሀሴት ይሞላሉ። ግድቡን እንደጣሰ ውሃ መላው ሰውነቴ በተስፋ ሲጠመቅ እንባ ያንቀኛል። ለካ የእሷ መኖር በነፍሴ ሰማይ የወጣችው ደማቅ ፀሀይ ነች። ብዙ ሰው ስለ እሷ ሳወራ እህትህ ናት አይለኝም። ፍቅረኛህ ነች ይለኛል። ናፍቆቷ ከአቅሜ በላይ ሲሆን ስቅስቅ ብዬ አልቅሼ አውቃለሁ። ለምን ተዋወቅን ብዬ እግዜርን ያማረርኩበት ቀን ብዙ ነው። ንጋት ላይ ድምጿን ሰምቼ ቀኔ ደምቆ ሲውል እንደእኔ የምትወደው ልጅ የለም ብዬ አመስግኜው አውቃለሁ። እሷ ረቂቅ ናት ነብሷ ብዙ ቅኔ አለው። . መኖርሽ ኩራቴ ልደትሽ ልደቴ ሰርክ ሰርኩን እንድታደም እንደ ዳዊት የቃል ድጋም ውብ ነብስሽ ገዳሜ እንደ ሳቅሽ አስገምግሜ ካለመኖር ያሳር እጣ ቀን ጎድሎብኝ እኔን ሳጣ አንቺ መጣሽ አገኘሁሽ ቀን ሞላልኝ - ነጋ ዘመን መኖር ሆነ የኔ - ውጥን ፪ ለድል የተራበ ሽንፈት የጠገበ በዘመን ተገፍቶ - ሀሴት የታዘለ የኔ ገላ አካል - አንቺ ጋ ነፍስ አለ የልቤ ውብ ቅንድብ አንች የነፍሴ ምኩራብ ሽፍንፍን አድርጌ - ሰስቼ ልውደድሽ ስቃይሽን ልውረስ - አንቺን ክፉ አይንካሽ መራብሽን ልራብ ህመምሽን ልጥገብ አንቺ የመውደድ ጥግ - የሰው መጀመሪያ የህይወቴ ሰንደቅ - ሰውነት ማሰሪያ አምላኬ አምላክሽ አምላክሽ አምላኬ በዘመን ስጦታው አንቺን ሰጠኝና ይኸው ሙሉ አረገኝ መኖሬ እንዲቀና .................. / / .................. ሩሐማዬ የኔ ደግ እህት እንኳን ተወለድሽልኝ! ዛሬ የአንቺ ልደት ብቻ አይደለም የኔም ልደት ነው አንቺ ባትኖሪ ምን ያህል ጎደሎ እንደምሆን ልነግርሽ የምችልበት ቃል ቢኖር ምንኛ በታደልኩ ግን አጣሁ። የኔ ደማቅ ኮከብ ጥንካሬዬ አንቺ ነሽ ብዙሃን እህት ልክ እንደእናት ናት ይላሉ። እኔ ግን በእሱ አልስማማም እህት ትንሿ እናት ናት። ነብስሽ ፣ ለፍቅር ፣ ለመውደድ ለደስታ የተሰጠች ስጦታ ነች። ባለፈው " ወንድምዬ በልደቴ ቀን እኮ ፈተና አለብኝ አያስጠላም? " ስትይኝ ቅር አለኝ። ለምንድነው ልደታችን ያላለችው ብዬ አሰብኩ። ሩ አንቺ ባትኖሪ እኮ ባዶ ነኝ። የኔ አንገታም 😂 የኔ ዶለዝ 😂 አብዝቼ እወድሻለው በህይወቴ ቦታ ካላቸው ሰዎች መድቤሻለሁ። የኔ ልዩ ሴት አለኝ የምለውን ሁሉ አጥቼ አንቺን ከጎኔ ባገኝ የምከፋ አይነት ሰው አይደለሁም። በቃ አጋነንክ ይሉኛል እንጂ አንቺ ለእኔ ሀገር ነሽ ፣ አለም ነሽ ፣ የደስታ ምንጩ ኩሬ ነሽ። ከዚህ በላይ ምን አለ የኔ ትንሿ እናት? ዘመንሽ ይባረክልኝ ! ሺህ አመት ኑሪልኝ የአንቺ መኖር የእኔ መቆም ተስፋ ነውና አቆያት ልውደዳት ብዬ ስፀልይ ሲራክም ይኖር ዘንድ ምክኒያት ይሁን ማለቴን እግዜሩ ሳይረዳ ይቀራል? ( አይቀርም ) እህት አትመሰገንም እንጂ መስቀሌን ስለተሸከምሽ ብዙ ምስጋና ነበረኝ ግን ተዝቆ የማያልቅ ውዴታዬን እንቺ እወድሻለሁ። ዛሬ ልደታችን ነው። ጨረቃዋ ሳትቀር ይላታል። ካላላትም እንደ ገጣሚው እናቷን እንላታለን። እናቷን ጨረቃ😂 መልካም ልደት ለእንቁዋ እህቴ ለሩሐማ ማሾ ሀይሌ❤ ቅዳሜ መስከረም 8 2014 ዓ.ም Each day provides its own gifts.
Brave Generation - мотивация
Динамика подписчиков
+0.0% за 30 дней
Текущие
95
Месяц назад
95
Средний рост
+0 / день
Обновлено
6 часов назад

Отзывы о канале Brave Generation - мотивация

Авторизуйтесь, чтобы оставить отзыв

Только зарегистрированные пользователи могут делиться своим мнением.

Пока нет отзывов

Станьте первым, кто поделится своим впечатлением об этом ресурсе!

Похожие ресурсы

𝙀𝙬𝙣𝙞𝙖𝙡 𝙀𝙙𝙞𝙩𝙨 – канал с профессиональными видео-монтажами и эдитами в Telegram.

Канал

Канал Cockpit с сигналами и анализом NIFTY и BANKNIFTY. Новости рынка, опционы и обсуждения для успешной торговли.

Канал

Оригинальные цитаты и мотивирующие фразы. Вдохновение каждый день в удобном Telegram-канале.

Канал
Переход на светлую тему
Главная Каталог Подборки Блог Вход