и посмотреть медиа
Dilla University - официал
и посмотреть медиа
Dilla University Official — официальный канал университета. Новости, расписание и учебные ресурсы.
Dilla University Official — официальный канал университета. Новости, расписание и учебные ресурсы.
🏫 Dilla University Official — официальный Telegram-канал University of the Green Land в Эфиопии. Актуальные новости, расписание и материалы.
Здесь публикуются объявления, лекции, задания и события кампуса. Полезно для студентов и преподавателей.
🌿 Фокус на зеленых инициативах и академической жизни. Регулярные обновления держат в курсе всех важных событий университета.
"በቀናነት ከሰራን፣ ችግሮች ሲኖሩ በመቀራረብ ከፈታን፣ ተቋማችንን ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ማድረግ እንችላለን" - ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) ============**************============ ዲዩ: ነሐሴ 05/2018ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ካውንስል በየዘርፉ የቀረቡ የ2018ዓ.ም የእቅድ ክንውን ሪፖርትን ገምግሟል። በበጀት ዓመቱ በመማር ማስተማር ዘርፍ፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት፣ በዲጅታላይዜሽን ረገድ፣ አጠቃላይ መሠረተ ልማት ማስፋፊያ ስራዎች፣ የጤና ዘርፍ ተግባራት፣ በግንባታ ፕሮጀክቶች አፈፃፀምና በሌሎችም ዘርፎች ላይ የተከናወኑ ተግባራት ለካውንስሉ ቀርበዋል። የካውንስል አባላት በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ የተለያዩ ሀሳብና አስተያዬት ሰጥተዋል። አገልግሎት ያቆሙ መሳሪያዎችን ወደ አገልግሎት በመመለስ ረገድ የተሰራው ስራ፣ የስማርት መማሪያ ክፍሎች ግንባታ፣ በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ የተመዘገቡ ውጤቶችና የነበሩ የጉድኝት ተግባራት የሚበረታቱ ስለመሆናቸው የካውንስሉ አባላት አንስተዋል። የመምህራን የቤት ችግርን ለመቅረፍ የተጀመሩ ስራዎች እንደመኖራቸው መጠን በአጭር ጊዜ ለመፍታት እንዲሰራ፣ አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍና ክትትል እንዲደረግም የካውንስል አባላቱ ጠይቀዋል። የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ቶሎሳ ዳዲ (ዶ/ር) በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ከካውንስሉ የተነሱ ሀሳቦችን እንደ ግብዓት በመውሰድ ቀሪ ተግባራቶቻችን ላይ በማከል የተሻለ ተቋማዊ አፈፃፀም እንዲኖር ጠንክረን እንሰራለን ብለዋል። የትምህርት ሴክተር ሪፎርምን መሬት የማውረድ ስራ በትኩረት መሠራት እንዳለበት የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፣ ከሪፎርሞቹ አንዱ የሆነው የትኩረት አቅጣጫ እና የልየታ ስራ ላይ የቀሩ ተግባራትን መከወን የአዲሱ የትምህርት ዘመን ቀዳሚ ስራ መሆኑን ገልፀዋል። ቤተሙከራዎች እና ፕሮግራሞቻችንን በሀገር አቀፍ እና በዓለምአቀፍ ደረጃ እውቅና እንዲያገኙ ለማድረግ በትኩረት መስራት ይኖርብናልም ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ። የራስ ገዝነት ስራ ቀጣዩ የቤት ስራችን ሊሆን ይገባል ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ ወደዚህ ለመግባት በሚያስችሉ አመቺ ሁኔታዎች ላይ ማተኮር ይገባል ብለዋል። የመማሪያ ክፍሎችን ዲጂታላይዝ ለማድረግ መሠረተ ልማቶችን ለማሟላት የተጀመረው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አክለዋል። ከመምህራን ቤቶች ጋር ተያይዞ ከካውንስሉ ለተነሳው ጥያቄ፣ የመምህራንን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል። በቀናነት ከሰራን፣ ችግሮች ሲኖሩ በመቀራረብ ከፈታን፣ ተቋማችንን ወደተሻለ ደረጃ ከፍ ማድረግ እንችላለን ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ የታቀዱ ስራዎች ሁሉ ከግብ እንዲደርሱ የዩኒቨርሲቲው ካውንስል ድጋፉን እንድያጠናክር ጥሪ አቅርበዋል። የኮምፒውተር ቤተ-ሙከራዎች ደረጃቸውን የጠበቁ እንዲሆኑ በአዲስ መልክ ለማደራጀት እየተሰራ እንደሚገኝ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ፣ የበይነ መረብ ትምህርት ስርዓትን እውን ለማድረግ በተቋም ደረጃ ስቱዲዮ ለመገንባት ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝም አብራርተዋል። የፀጥታ ስራዎችን የበለጠ የማጠናከር፣ አዲሱ ሆስፒታልን ወደ ስራ የማስገባት ስራ የቀጣይ ጊዜያት የትኩረት ዘርፎች አካል ስለመሆናቸውም አንስተዋል። የአመራር ብቃትን የበለጠ ለማጎልበት እንዲሁም በሁሉም ዘርፎች ላይ የተለያዩ ተከታታይ ስልጠናዎች እንደሚዘጋጁ ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል። በዩኒቨርሲቲው የተጀመሩ ነባር ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ከወትሮ በተለየ መልኩ እንደሚሰራም አውስተዋል። በዩኒቨርሲቲው ስር ያሉ የምርምር ጣቢያዎች አስፈላጊው ሁሉ መሠረተ ልማት እንዲሟላላቸው መስራት እንደሚያስፈልግም ፕሬዝዳንቱ አንስተዋል። በሪፖርቱ ላይ የቀረቡ መልካም ስራዎችን ለማስቀጠል፣ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይም በየደረጃው ያለው የዩኒቨርሲቲው አመራር በመቀናጀት ለተሻለ አፈፃፀም አብሮ እንዲሰራ ጥሪ ቀርቧል። ===###=== #የአረንጓዴው_ምድር_ዩኒቨርሲቲ
Открыть канал и посмотреть медиаТолько зарегистрированные пользователи могут делиться своим мнением.
Станьте первым, кто поделится своим впечатлением об этом ресурсе!
Анонимный бот для студентов TUIT: отправляйте сообщения, confessions и истории анонимно.
Пионерский канал CA в Индии с 2016: накопленные материалы, заметки от студентов и факультетов. #CABornToFight
Канал с короткими текстами о жизни, времени и повседневных моментах.