и посмотреть медиа
EBS TV - эфиопское ТВ
и посмотреть медиа
Канал эфиопского телевидения EBS: новости, программы, шоу и прямые трансляции.
Канал эфиопского телевидения EBS: новости, программы, шоу и прямые трансляции.
📺 EBS TV — ведущий эфиопский телеканал в Telegram. Доступ к новостям, ток-шоу, развлекательным программам и культурному контенту.
📰 Ежедневные выпуски новостей: политика, экономика, спорт Эфиопии и Африки. Плюс эксклюзивные интервью, документальные фильмы и живые эфиры.
🎭 Разнообразие: от образовательных передач до музыки и сериалов. Удобно для диаспоры и любителей эфиопской культуры — смотрите в любое время без кабельного ТВ.
#NationalDialogue🇪🇹 የሰንደቅ አላማ ጉዳይ "አሁን ያለው ይቀጥል" የሚለው አስማምቶ፣ "አርማው አካታች በሆነ መልኩ ለወደፊት ይታይ" የሚል አማራጭ ሀሳብ ቀረበለት። 👉 ለኢትዮጵያ "ብሔራዊ ቋንቋ ለጊዜው አያስፈልግም" ፤ ካስፈለገ ለወደፊት ይኖራል በሚል ተመካካሪዎችን አስማምቷል። 👉 አምስት ቋንቋዎች የፌዴራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ፣ ሌሎችም መስፈርት ወጥቶላቸው ለወደፊት እንዲታዩ ተብሏል። ከ8ቱም ቡድኖች በተመረጡ አጠናቃሪዎች የተዋቀረው አዘጋጅ ቡድን እያንዳንዳቸው 500 ሰዎችን ከያዙ 8 ቡድኖች ተቀብሎ ያጣጣማቸውን፣ ድግግሞሽ እንዳይኖር ያስወገደላቸውን የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች አዘጋጅቶ የ8ቱንም ቡድኖች ምክረ ሀሳቦች የያዘ ቃለጉባዔ ለ8ቱም ቡድኖች ዛሬ አቅርቧል። ተመካካካሪዎች በተለያዩ ቡድኖች ተደራጅተው ሀሳብ ከማመንጨት እስከ በሀሳቦቹ መከራከር ድረስ ከመከሩባቸው ስምንት አጀንዳዎች መካከል የሀገር ግንባት አጀንዳ አንዱ ሲሆን፣ በዚሁ አጀንዳ በዛሬው ቃለጉባዔ ከተነሱት ምክሮች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው። ብሔራዊ ቋንቋ ፦ የቋንቋ ጉዳይን በተመለከተ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ይኑራት? ወይስ አይኑራት? እና ይኑራት ከተባለ ደግሞ አማርኛ ይሁን፣ አፋን ኦሮሞ ይሁን የሚሉ ምክረ ሀሳቦች ከተመካካሪዎች ቀርበው ሲያከራክሩ ሰንብተዋል። ከ8ቱም ቡድኖች የተመረጡ 120 አባላት ያሉት በምክረ ሀሳቦቹ አንድ ወጥ አጀንዳ የሚያዘጅ ቡድን እያንዳቸው 500 ሰዎች ለያዙት ቡድኖች 8ቱም ቡድኖች ባነበበው ቃለጉባዔ መሰረት ደግሞ፣ "አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ብሔራዊ ቋንቋ አያስፈልገንም" የሚለው ስምምነት እንደተደረሰበት የአንድ አጀንዳው ተሳታፊ ነግረውናል። "ሲያስፈልግ እንደ ሁኔታው ታይቶ ካሉት ቋንቋዎች አስፈላጊው ሊደረግ ይችላል" የሚል ምክረ ሀሳብም ተያይዞ መቅረቡን ገልጸዋል። የሥራ ቋንቋ ፦ የፌዴራል የሥራ ቋንቋን በተመለከተ ደግሞ፣ መጀመሪያ አምስት ቋንቋዎች ቀርበው፣ በኋላ ደግሞ ወደ 13 ቋንቋዎች የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ ተመካካሪዎች ምክረ ሀሳብ ሲያቀርቡ ነበር። በተነበበው ቃለጉባዔ ደግሞ፣ - አማርኛ - አፋን ኦሮሞ - ትግርኛ - አፋርኛ - ሶማሊኛ የፌዴራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ፣ በቀጣይነት ሌሎችም እንዲከቱ የሚል ሀሳብ በአመዛኙ ተመካካሪዎች መቅረቡን ተሳታፊው ተናግረዋል። እንዲሁም ፦ - ወላይትኛ - ሲዳምኛ - ጉራግኛ - ከምባትኛ - አገውኛ - ከፊቾ/ከፍኛ - ጋሞኛ ቋንቋዎችም መስፈርት ወጥቶላቸው "እንደተናጋሪው ብዛት መስፈርት እየታዬ" ለወደፊት የፌዴራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ የሚል አማራጭ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል። የሰንደቅ አላማ ፦ የሰንደቅ አላማን ጉዳይ በተመለከተ ተመካካሪዎች አሁን ያለው ይቀጥል፤ አርማው ይቀየር፣ ሲቀየር ደግሞ የሕዳሴ ግድብ ይሁን፣ የዓድዋ ድል፣ የእርግብና ሌሎች ይሁን የሚሉ አማራጭ ምክረ ሀሳቦች ከጉባያተኞች ቀርበው ነበር። ዛሬ በተነበበውና አስተያየት ተሰጥቶበት ነገ ይጠናቀቃል በተባለው ቃለጉባዔ ደግሞ፣ "አሁን ያለው ይቀጥል እና አርማው አካታች በሆነ መልኩ ለወደፊት ይታይ" የሚሉ ሁለት ምክረ ሀሳቦች መቅረባቸው ተገልጿል። "አካታች በሆነ መልኩ" ሲባል "ህዝቡ ለወደፊት ቀርቦ እንዲወስን" መባሉ ተመልክቷል። ብሔራዊ መዝሙር፦ ኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን በተመለከተ የተለያዩ ምክረ ሀሳቦች ሲቀርቡ እንደነበር ይታወቃል። በዛሬው ውሎ ደግሞ፣ "ብሔራዊ መዝሙር እንዳለ ይቀጥል" የሚል ምክረ ሀሳብ መቅረቡን ተመካካሪዎች ተናግረዋል። የክልሎችን መዝሙር በተመለከተም፣ "መዝሙሩ ይኑር፤ የክልሉን ነባራዊ ሁኔት አካታች ያድርግ፣ በአላስፈላጊት የገቡ መብትን የሚነኩ ግጭት የሚቀሰቅሱ ሀሳቦች ካሉ ይታረሙ" የሚል ምክረ ሀሳብ መቅረቡም ተገልጿል። ከዚህ አጀንዳ በተጨማሪ ሌሎች አጀንዳዎችም የተለያዩ ምክረ ሀሳቦች የቀረቡላቸው ሲሆን፣ ይህን ጨምሮ የሁሉም የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች ሰነድ አስተያየት ካለ ተካቶባቸው ነገ ለ4ሺሕው ጉባያተኞች ቀርበው ለመጨረሻ ጊዜ ይሰነዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ቲክቫህ ኢትዮጵያም ጉዳዮቹን ተከታትሎ መረጃ የሚያቀርብ ይሆናል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
Открыть канал и посмотреть медиаТолько зарегистрированные пользователи могут делиться своим мнением.
Станьте первым, кто поделится своим впечатлением об этом ресурсе!
RT News - новости мира без цензуры. Фокус на правде и критическом мышлении.
Канал о Москве, чтобы не пропустить интересное и важное в столице.