Logo
TGCATALOG
Catalog Collections Blog
EBS TV - эфиопское ТВ

EBS TV - эфиопское ТВ

Канал эфиопского телевидения EBS: новости, программы, шоу и прямые трансляции.

No ratings
125
09.09.2026
125
09.09.2026
No ratings
125
09.09.2026
Safe redirect via bot
О канале

Канал эфиопского телевидения EBS: новости, программы, шоу и прямые трансляции.

Подписчиков 4,548
Тематика News
Язык English
Ссылка t.me/etv_newss
Description

📺 EBS TV — ведущий эфиопский телеканал в Telegram. Доступ к новостям, ток-шоу, развлекательным программам и культурному контенту.

📰 Ежедневные выпуски новостей: политика, экономика, спорт Эфиопии и Африки. Плюс эксклюзивные интервью, документальные фильмы и живые эфиры.

🎭 Разнообразие: от образовательных передач до музыки и сериалов. Удобно для диаспоры и любителей эфиопской культуры — смотрите в любое время без кабельного ТВ.

Latest posts

EBS TV - эфиопское ТВ
EBS TV - эфиопское ТВ
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
#RobelGetachew👏 በዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በሀገር አቀፍ ደረጃ ከመላው ተፈታኞች ከፍተኛውን ሁለተኛ ውጤት ያመጣው በሀዲያ የሚገኘው የሊችጎጎ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪው ሮቤል ጌታቸው ሲሆን ያስመዘገበው ውጤት 590.08 ነው። #Lichgogo #Hadiya #ከሀገርተስፋዎች👏 @tikvahethiopia
EBS TV - эфиопское ТВ
EBS TV - эфиопское ТВ
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
#JalalGirma👏 የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ጃላል ግርማ በ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተና 591. 6 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል። #ODA_SPECIAL_BOARDING_SCHOOL @tikvahethiopia
EBS TV - эфиопское ТВ
EBS TV - эфиопское ТВ
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
#JalalGirma👏 የኦሮሚያ ልማት ማህበር (ኦልማ) ልዩ አዳሪ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ጃላል ግርማ በ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ማጠናቀቂያ ፈተና 591. 6 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል። #ODA_SPECIAL_BOARDING_SCHOOL @tikvahethiopia
EBS TV - эфиопское ТВ
EBS TV - эфиопское ТВ
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
በትግራይ ክልል በ2018 ዓ.ም. 33 ሴቶች በግፍ መገደላቸው ተገለጸ። እየተጠናቀቀ ባለው 2018 ዓ.ም. ብቻ በትግራይ 33 ሴቶች በግፍ መገደላቸውን የትግራይ ሴቶች ማህበር አስታወቀ። ማህበሩ የተጎጂዎች ቤተሰቦች ፍትህ እንዲያገኙና የሕግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገልጿል። ይህ መረጃ የተሰማው በቅርቡ በመቐለ ከተማ የዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ጉዳይ ላይ የተላለፈውን የፍርድ ቤት ውሳኔ በመቃወም የሴቶች መብት ተሟጋቾች እያካሄዱ ካሉት እንቅስቃሴዎች ጋር በተያያዘ ነው። በመቐለ ከሁለት ዓመት በፊት በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደለችውን ዘውዱ ሃፍቱን ግድያ በተመለከተ፣ የመቐለ ማዕከላዊ ፍርድ ቤት ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ተከሳሾቹ በነፃ እንዲለቀቁ ውሳኔ ሰጥቷል። የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ዘጠኝ የሴቶች መብት ተሟጋች ሲቪል ማህበራት የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። የመቐለ ዓቃቤ ሕግም የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ማቅረቡ ታውቋል። በተጨማሪም የዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ጉዳይ ላይ የተላለፈው ውሳኔ " ኢ-ፍትሃዊ ነው " በሚል በርካታ ሴቶች የዘንድሮውን የአሸንዳ በዓል ጥቁር ልብስ በመልበስ ለማሰብ የሚጠይቅ እንቅስቃሴ ጀምረዋል። ተሳታፊዎቹ ሙሉ ጥቁር ልብስ በመልበስ " የዘንድሮ የአሸንዳ አምባሳደር ዘውዲ ናት፤ ፍትህ በግፍ ለተገደለችው ዘውዲ " የሚሉ እና የሴቶች መብት እንዲከበር የሚጠይቁ መልዕክቶችን በማስተላለፍ ላይ ናቸው። እንቅስቃሴው በተለይም በማህበራዊ ሚዲያ ገፆች በስፋት እየተሰራጨ ይገኛል። የትግራይ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ በበኩሉ እንቅስቃሴውን በመቃወም፣ የአሸንዳ በዓል ባህሉንና እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር የሚያስገነዝብ መግለጫ ቢያወጣም፣ የሴቶቹ የተቃውሞ እንቅስቃሴ በማህበራዊ ሚዲያ ቀጥሏል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 14 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
EBS TV - эфиопское ТВ
EBS TV - эфиопское ТВ
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
#NationalDialogue🇪🇹 የሰንደቅ አላማ ጉዳይ "አሁን ያለው ይቀጥል" የሚለው አስማምቶ፣ "አርማው አካታች በሆነ መልኩ ለወደፊት ይታይ" የሚል አማራጭ ሀሳብ ቀረበለት። 👉 ለኢትዮጵያ "ብሔራዊ ቋንቋ ለጊዜው አያስፈልግም" ፤ ካስፈለገ ለወደፊት ይኖራል በሚል ተመካካሪዎችን አስማምቷል። 👉 አምስት ቋንቋዎች የፌዴራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ፣ ሌሎችም መስፈርት ወጥቶላቸው ለወደፊት እንዲታዩ ተብሏል። ከ8ቱም ቡድኖች በተመረጡ አጠናቃሪዎች የተዋቀረው አዘጋጅ ቡድን እያንዳንዳቸው 500 ሰዎችን ከያዙ 8 ቡድኖች ተቀብሎ ያጣጣማቸውን፣ ድግግሞሽ እንዳይኖር ያስወገደላቸውን የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች አዘጋጅቶ የ8ቱንም ቡድኖች ምክረ ሀሳቦች የያዘ ቃለጉባዔ ለ8ቱም ቡድኖች ዛሬ አቅርቧል። ተመካካካሪዎች በተለያዩ ቡድኖች ተደራጅተው ሀሳብ ከማመንጨት እስከ በሀሳቦቹ መከራከር ድረስ ከመከሩባቸው ስምንት አጀንዳዎች መካከል የሀገር ግንባት አጀንዳ አንዱ ሲሆን፣ በዚሁ አጀንዳ በዛሬው ቃለጉባዔ ከተነሱት ምክሮች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው። ብሔራዊ ቋንቋ ፦ የቋንቋ ጉዳይን በተመለከተ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ቋንቋ ይኑራት? ወይስ አይኑራት? እና ይኑራት ከተባለ ደግሞ አማርኛ ይሁን፣ አፋን ኦሮሞ ይሁን የሚሉ ምክረ ሀሳቦች ከተመካካሪዎች ቀርበው ሲያከራክሩ ሰንብተዋል። ከ8ቱም ቡድኖች የተመረጡ 120 አባላት ያሉት በምክረ ሀሳቦቹ አንድ ወጥ አጀንዳ የሚያዘጅ ቡድን እያንዳቸው 500 ሰዎች ለያዙት ቡድኖች 8ቱም ቡድኖች ባነበበው ቃለጉባዔ መሰረት ደግሞ፣ "አሁን ባለንበት ነባራዊ ሁኔታ ብሔራዊ ቋንቋ አያስፈልገንም" የሚለው ስምምነት እንደተደረሰበት የአንድ አጀንዳው ተሳታፊ ነግረውናል። "ሲያስፈልግ እንደ ሁኔታው ታይቶ ካሉት ቋንቋዎች አስፈላጊው ሊደረግ ይችላል" የሚል ምክረ ሀሳብም ተያይዞ መቅረቡን ገልጸዋል። የሥራ ቋንቋ ፦ የፌዴራል የሥራ ቋንቋን በተመለከተ ደግሞ፣ መጀመሪያ አምስት ቋንቋዎች ቀርበው፣ በኋላ ደግሞ ወደ 13 ቋንቋዎች የኢትዮጵያ የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ ተመካካሪዎች ምክረ ሀሳብ ሲያቀርቡ ነበር። በተነበበው ቃለጉባዔ ደግሞ፣ - አማርኛ - አፋን ኦሮሞ - ትግርኛ - አፋርኛ - ሶማሊኛ የፌዴራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ፣ በቀጣይነት ሌሎችም እንዲከቱ የሚል ሀሳብ በአመዛኙ ተመካካሪዎች መቅረቡን ተሳታፊው ተናግረዋል። እንዲሁም ፦ - ወላይትኛ - ሲዳምኛ - ጉራግኛ - ከምባትኛ - አገውኛ - ከፊቾ/ከፍኛ - ጋሞኛ ቋንቋዎችም መስፈርት ወጥቶላቸው "እንደተናጋሪው ብዛት መስፈርት እየታዬ" ለወደፊት የፌዴራል የሥራ ቋንቋ እንዲሆኑ የሚል አማራጭ ምክረ ሀሳብ ቀርቧል። የሰንደቅ አላማ ፦ የሰንደቅ አላማን ጉዳይ በተመለከተ ተመካካሪዎች አሁን ያለው ይቀጥል፤ አርማው ይቀየር፣ ሲቀየር ደግሞ የሕዳሴ ግድብ ይሁን፣ የዓድዋ ድል፣ የእርግብና ሌሎች ይሁን የሚሉ አማራጭ ምክረ ሀሳቦች ከጉባያተኞች ቀርበው ነበር። ዛሬ በተነበበውና አስተያየት ተሰጥቶበት ነገ ይጠናቀቃል በተባለው ቃለጉባዔ ደግሞ፣ "አሁን ያለው ይቀጥል እና አርማው አካታች በሆነ መልኩ ለወደፊት ይታይ" የሚሉ ሁለት ምክረ ሀሳቦች መቅረባቸው ተገልጿል። "አካታች በሆነ መልኩ" ሲባል "ህዝቡ ለወደፊት ቀርቦ እንዲወስን" መባሉ ተመልክቷል። ብሔራዊ መዝሙር፦ ኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን በተመለከተ የተለያዩ ምክረ ሀሳቦች ሲቀርቡ እንደነበር ይታወቃል። በዛሬው ውሎ ደግሞ፣ "ብሔራዊ መዝሙር እንዳለ ይቀጥል" የሚል ምክረ ሀሳብ መቅረቡን ተመካካሪዎች ተናግረዋል። የክልሎችን መዝሙር በተመለከተም፣ "መዝሙሩ ይኑር፤ የክልሉን ነባራዊ ሁኔት አካታች ያድርግ፣ በአላስፈላጊት የገቡ መብትን የሚነኩ ግጭት የሚቀሰቅሱ ሀሳቦች ካሉ ይታረሙ" የሚል ምክረ ሀሳብ መቅረቡም ተገልጿል። ከዚህ አጀንዳ በተጨማሪ ሌሎች አጀንዳዎችም የተለያዩ ምክረ ሀሳቦች የቀረቡላቸው ሲሆን፣ ይህን ጨምሮ የሁሉም የአጀንዳ ምክረ ሀሳቦች ሰነድ አስተያየት ካለ ተካቶባቸው ነገ ለ4ሺሕው ጉባያተኞች ቀርበው ለመጨረሻ ጊዜ ይሰነዳሉ ተብሎ ይጠበቃል። ቲክቫህ ኢትዮጵያም ጉዳዮቹን ተከታትሎ መረጃ የሚያቀርብ ይሆናል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ #TikvahEthiopiaFamilyAA @tikvahethiopia
EBS TV - эфиопское ТВ
EBS TV - эфиопское ТВ
🔒Открыть пост
и посмотреть медиа
"የውህድ ማንነት" ጉዳይ በሀገራዊ ምክክሩ "የውህድ ማንነት" ጉዳይ በፓርቲ ደረጃ መቅረቡን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የገለጹ የዚሁ አጀንዳ ተመካካሪ፣ "የሁለት 'ውህድ ማንነት' ያላቸው ሰዎች" እንዳሉ ተመላክቶ "አሁን ያለው አሰራር ለአገልግሎት መታወቂያ ሲጠየቁ በአንድ ማንነት ብቻ እንዲጠሩ ስለሚያስገድዳቸው 'ብሔር የለኝም ውህድ ነኝ' የማለት መብት ሊኖራቸው ይገባል" የሚል ምክረ ሀሳብ ቀርቦ ብዙ ተቃውሞ ቢያጋጥመውም ከሥራ ቡድኑ ወደ ሀሳብ አደራጅ ቡድኑ ተሻግሮ እንደነበር ገልጸዋል። "ይህ የኢትዮጵያውያን እሴት አይደለም። ሰው በአባቱ ነው የሚጠራው። 'ውህድ' የምትሉት ነገር ለባዕድ እሴት በር የሚከፍት ነው" በሚል ተቃውሞ ሲነሳበት፣ "'ውህድ ማንነት' የሚለው ቀርቶ 'ውህድ የብሔር ማንነት'" በሚል ሀሳቡ አልፎ እንደነበር ተናግረዋል። 120 አባላት ባሉት ሀሳብ አዘጋጅ ቡድን ታይቶ ግን ቡድኑ ትናንት ለ500 ሰዎች ሪፖርት ሲያቀርብ፣ ጉዳዩ ለምን እንዳለፈ ጠይቆ፣ "'እንዲያውም ከሰነዱ ይውጣ' ብሎ እጅ እንዲወጣ ተደርጎ አብዛኛው ነቅፎ እጅ አወጣ። ያን ሀሳብ የሚደግፉ ጥቂት ሰዎች እዚህ ድረስ የመጣን ሀሳብ 'በአድማ ልትቀለብሱ አትችሉም' በማለታቸው ስምምነት ያልተደረሰበት ምክረ ሀሳብ ሆኖ እንዲያልፍ ተደርጓል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ቲክቫህ ኢትዮጵያ አዲስ አበባ ነሐሴ 12 ቀን 2018 ዓ/ም @tikvahethiopia
EBS TV - эфиопское ТВ
Subscriber dynamics
+-0.1% last 30 days
Current
4,548
Month ago
4,554
Average growth
+0 / day
Updated
1 day ago

Reviews for channel EBS TV - эфиопское ТВ

Log in to leave a review

Only registered users can share their opinion.

No reviews yet

Be the first to share your impression of this resource!

Similar resources

News of politics, economics and agribusiness from a liberal position. The main voice of liberalism in Brazil.

Channel

ReforumSpaceVilnius: a space for people, ideas and projects. Support for journalists and activists.

Channel

Information about Corona adapted for young people. Facts and clarifications.

Channel
Switch to Light Theme
Home Catalog Collections Blog Login