и посмотреть медиа
Brave Generation - мотивация
и посмотреть медиа
Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.
Мотивационный канал Brave Generation с цитатами, видео и историями для силы духа и преодоления.
Brave Generation предлагает ежедневную дозу мотивации: вдохновляющие цитаты, видео с реальными историями успеха, советы по развитию силы воли. Идеально для тех, кто стремится к личностному росту и преодолению трудностей. Контент помогает зарядиться энергией и двигаться вперед.
#ማምሻ_አራት ለምጄሽ ነበር መሰለኝ፣ብዙ የማቅሽ ይመስለኛል፡፡ ግን እኮ አላቅሽም፤ጥቂት ማዉራት ትንሽ መግባባት ብቻ ነበር ማህላችን፡፡ ያ ሳታቂኝ ያወኩሽ ሳታዪኝ ያየሁሽ ቀን መልክሽ ትዝ ይለኛል መንገድ ማህል ቆሜ የተደናገርኩበት፡፡ ታዲያ ምን ለመድኩሽ ጥቂት አይደል ከዛስ ያየሁሽ፡፡ ግን እኮ ለምጄሻለዉ፤ሩቅ ሆኖ ቅርብ የሚመስለዉ ድምጽሽ ጆሮዬ ስር ሰርክ ያቃጭላል፣ተጠግቼዉ እንኳን የማላቀዉ ገላሽ ጠረኑን የማዉቀዉ ሁሌ የምደባብሰዉ ይመስለኛል… አንቺን ሳስብ እዛ ማዶ ከተራራዉ ጀርባ ገብቶ ከተሰወረዉ አለም ወስዶ ይመልሰኛል፣ስመለስ ግን አንቺ የለሽም፣ደግሞም እንደማላቅሽ ትሆኚብኛለሽ… ታዲያ ካላወኩሽ መምጣትሽን ሳላዉቀዉ ለምን መሄድሽ አመመኝ…..ምጽዋትን ፈልጎ እንዳጣ የኔ ቢጤ፣በርሃ ማህል እንደተጠማ እጽዋት፣ባክኖ መና እነደቀረ ገበሬ ለምን ተሰማኝ…. እንጃ እስቲ ዉዴ አንቺን ልጠይቅሽ… ለምን ይሆን ቅርቤ መስለሽ ተሩቅ ያለሽ ከማልደርሰዉ ተዚያ ማዶ ተሰዉረሽ ተዚያ ማዶ ከአድመሱ ስር ከመንፈሴ ተሸሽገሽ ከመንፈሴ ያለሽ መስሎኝ ያስቀመጥኩሽ ስፈልግሽ ሳፋልግሽ አለሁ ካላልሽ በፊቱንም ከኔ አልነበርሽ ግና ዉዴ ስፈልግሽ ከኔ ካልሆንሽ ምላሽ ስጪኝ ለመሄድሽ ✍ይል #yilo15 @bravegenbyyil
Открыть канал и посмотреть медиаሰለ ድምጻዊ አለማየሁ እሸቴ (በእውቀቱ ስዩም) አለማየሁ እሸቴ በአጸደ- ስጋ አብሮን በነበረበት ጊዜ በተረብም በቁም ነገርም ሳነሳው ቆይቻለሁ ፤ እና የሚከተሉትን ቃላት የምጽፈው “ የሞተ ሰው አንገቱ ረጅም ነው” የሚለውን ልማድ ለመከተል አይደለም :: አለማየሁ እሽቴ, አባቴ ከሚወዳቸው ዘፋኞች እንዱ ነበር:: “ አይዘራፍ እያሉ” “ ከሰው ቤት እንጀራ” የተባሉትን ፤ የልጅነቴን ትዝታ ቀስቃሽ ዘፈኖች ፥ በቅርቡ ዩቲዩብ ላይ ፈልጌ አጣሁዋቸው :: አለማየሁ የፊልም አፍቃሪ እንደነበር ሰምተናል ፤ የወጣትነት ህይወቱም ሲኒማ- መራሽ ነበር፤ የሆነ ጊዜ ላይ አሌክስ ሂልተን ሆቴል ገባ፤ በሚዘናፈለው ጠጉሩ ላይ የቴክሳሰስ ባርኔጣ ገድግዷል ፤ ከወደ ቁርጭምጭሚቴ የሚሰፋ ቦላሌ ለብሷል፤ አግሩን የመመገቢያ ጠረቤዛ ላይ እግሩን አንፈራጦ በመቀመጥ ሲጃራ ማጤ ስ ጀመረ፤ አስተናጋጁ እግሩን እንዲያወርድ ጠየቀው ፤ እምቢ አለ፤ ዘበኛ ተጠርቶ መጣ፤ አሌክስ ፊሻሌ ሽጉጥ አወጣና ተኩሶ የዘበኛውን ኮፍያ አወለቀው ፤ ብዙ ሳይቆይ ፈጥኖ ደራሽና የክቡር ዘበኛ ሂልተን ሆቴልን ከበበው፤ አሌክስ ካዛንቺስ አካባቢ ሲግጥ የቆየውን ፈረሱን በፉጨት ጠራው:: ከዝያ “ እንዳሞራ “ ኮርቻው ላይ ፊጥ ካለ በሁዋላ ጋልቦ አመለጠ፤ ፈረስ የጠራበትን ፉጨቱን ወደ እንጉርጉሮ አሳደገው ፤ በለስ የቀናው ዘፋኝ ሆነ:: አሁን ያወጋሁት እልም ያለ ፈጠራ መሆኑን ተማምነን ወደ ቁምነገሩ እንሂድ:: አሌክስ ከሚጥም ድምጹ ባሻገር ዘናጭ ፤ ከፍተኛ በራስ መተማመን ያለው ሰው ነበር ፤ እጣፈንታ በብዙ ነገር አዳልታለታለች:: ተቸግሮ አልለመነም:: የሆነ ጊዜ ባለስልጣን ሆኖ ያቅሙን ያክል ህዝብ ነድቷል :: አርባ ምናመን አመት በሞቅ ትዳር ቆይቷል፤ ይህንን ያክል ዘመን ባንዲት ወይዘሮ እቅፍ ተወስኖ መቆየት በዘፋኝ አለም ብርቅ ነው ፤ አሌክስ በትዳር የቆየበትን ጊዜ ያክል ኬኔዲ መንገሻ በሕይወት አልቆየም:: ሙሉቀን መለሰ የሚያደንቀው ብቸኛ ዘፋኝ የጋሽ እሸቴን ልጅ ነው:: አለማየሁ በዘመናችን ካሉ ዘፋኞች የጎሳየ ተስፋየ አድናቂ መሆኑን ነግሮኛል:: “ የወይን አረጊቱ” “፥ አዲሳበባ ቤቴ’ ፥ “ አምባሰል “ እንደ ጥንቱ መስሎኝ””፥ ልተለየሽኝም “ ታሪክሽ ተጽፏ ል” የሚሉት ዘፈኖቹ ዘመን አልሻራቸውም፤ በጸጋየ ወይን ገብረመድህን( ደብተራው) የተደረሰው “ ያ ጥቁር ግስላ” የተሰኘው ዘፈኑ ራሱን የቻለ አቢዮት ነው ማለት ይቻላል :: “ የአስር ሳንቲም ቆሎ ፤ ቁርጥም አደርግና “ እሚለው ዘፈኑ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከየት ወዴት እንደ ሄደ ያመላክታል ፤ ለካ አስር ሳንቲም ሙዝየም ከመግባቱ በፊት ይሄን ያህል ሙያ ነበረው :: “ ካጣን ምናባቱ እንብላ ሽንብራ የሰው እጅን ብቻ እንዳናይ አደራ “ የሚለውን ዘፈንስ እንዴት ይረሳል? በአሌክስ የጉርምስና ዘመን፥ ያጣ የነጣው ድሃ ሽምብራ ተመጋቢ ነበር፤ አንዳንዴ ዜጎች የድሮውን ቢናፍቁ ምክንያት አላቸው :: አሌክስ የተረፈው ሀብታም ልጅ ነበር ፤ በጉርምስና ዘመኑ አንዴ ለመሰደድ የወሰነው እንጀራ ለማደን ሳይሆን የሆሊውድ አክተር የመሆን ምኞቱን ለማርካት ነበር :: ቢሆንም ስለ ድህነት አብዝቶ በመዝፈን ድሀ- አደግ ዘፋኞችን ሳይቀር ይቦንሳል :: በተለይ ኮለኔል ግርማ ሐይሌ ከተባለ ደራሲ የተቀበላቸው እንጉርጉሮዎች ከምሾ በላይ ሆድ የሚያስብሱ ናቸው :: እዚህ ላይ “ ስቀሽ አታስቂኝ “ የሚለው ፒያኖውን የሚያስለቅስበት ዜማው ትዝ ይለኛል፤ የዘፈኑ ባለታሪክ የሙት ልጅ የሆነች ድሃ ናት:: ኑሮን ለማሸነፍ “ትፍጨረጨራለች” ፤ በመከራዋ ላይም ትስቃለች :: ይህ በእንዲህ እያለ ወንድምየው ጣልቃ ገብቶ “ ስቀሽ አታስቂኝ “ ይላታል ፤ ““ ትፍጨረጨርያለሽ ወጉ አይቀር ብለሽ “ እያለ ያዳክማታል :: ጭራሽ “ ውሃ ጉድጉዋድ ግቢ የምየ ልጅ ባክሽ ” እያለ ይጎተጉታታል ፤ የሰው ልጅ ሁኔታ በጠቅላላው፤ በተለይ ደግሞ የኢትዮጵያ ሁኔታ ተስፋ አስቆርጦኝ ያውቃል ፤ “ስቀሽ አታስቂኝ”ን ስሰማ ግን እኔን ብሎ ተስፋ ቆራጭ እላለሁ፡: እንደዚህ ተስፋን ከጎድንና ከዳቢቱ እሚቆርጥ ዘፈን ገጥሞኝ አያውቅም :: ሰው ማለቂያ በሌለው ውድቀት መሀል እንኳን እየኖረ ተስፋና መጽናኛን የሚያማትር ፍጡር ነው ፤ ከአለማየሁ እሸቴ “ ስቀሽ አታስቂኝ “ ይልቅ የ አለማየሁ ሂርጶ” አታቀርቅሪ ቀን ያልፋል “ የሚለውን ዘፈን ይበልጥ የገነነው ለዚህ ይሆን ? @yilo15 @bravegenbyyil
Открыть канал и посмотреть медиа#ማምሻ_ሥስት አንቺና ይሁዳ እኮ አንድ ናቹ። እንዲያዉ ይሁዳ መልካም ሳይሆን ይቀራልን። ይሁዳኮ ገና ከመጀመሪያውም ተፅፎለታል የተካደዉ ወገን አዉቆታል፤አለአይደለ ያንቺ እየደባበሱ መዉጋት እያስታመሙ ማድማት። የይሁዳ እኮ የእምነት እዳ ነዉ። አለ አይደለ ያንቺ፣ ያለ እየመሰለ የሚሰወር እምነት፣ፍቅርን ተንተርሶ የሚያደማ እምነት። አይ ይሁዳ፣እሱ እኮ ተፈርዶበት ነዉ። አለሽ አይደል አንቺ አንቺው ፈራጅ የሆንሽ። ይሁዳ መክዳቱም ፊቱ ላይ ይነበብበት ነበር፣አስቀያሚ መልኩ ያሳብቅበታል። አንቺኮ ቆንጆ ነሽ፣ልቅም ያልሽ እንከን የማይወጣልሽ። ልጠይቅሽማ ... ይሁዳን ግን በተግባሩም በመልኩም በልጠሽዉ ምን ይሰማዉ ይሆን። እዉነት እሱ ብቻ በዳይ መስሎት አንገቱን ይደፋ ይሆን፤ወይስ...... ለካ የይሁዳም አምሳል ይፈቀራል (ድህረ ይሁዳ ነዉ ደሞ) በአምሳለ ይሁዳ ፈጥሮሽ ከሔዋን ዘር ሰርክ መሳሳም ነዉ በሚነክስ ከንፈር በሚናክስ ከንፈር ልብን በሚያደማ ተሸርፎ ተሸርፎ አንደሆነ ዖና የኔ መኖር ወዲህ ያንቺ መኖር ወዲያ ✍ይል @yilo15 @bravegenbyyil
Открыть канал и посмотреть медиа#ማምሻ_ሁለት መሆን ከብዶናል ……… መሆን ከብዶናል እያለ በተደጋጋሚ ድምጹን ከፍ አድርጎ ይናገራል… አንዴ ሰወች እብድ ነዉ ብለዉ ፈርጀዉት፣ የሱ መናገር ለነሱ መጮህ ሆኗል… ማንም የተረዳዉ የለም ለነሱ የሚሰማቸዉ ባዶ ጩኧት ነዉ፣ ለነገሩ እነሱስ በሱ አነጋገር መሆን የከበዳቸዉ አይደሉ… ስም ብቻን ይዘዉ የሚዞሩ፣እራሳቸዉን ሰዉ አሱን መሆን እንደከበዳቸዉ ያረዳቸዉን ግን እብድ ብለዉ የሰየሙ… ደሞኮ ያመዋል ይላሉ በጠና የታመሙት አነሱ ሆነዉ ሳለ… እሱ ግን ተረድቷቸዋል፣ስማቸዉ እንደከበዳቸዉ ገብቶታል፣መሆን ከብዷቸዋል… ባል ስሙን እንጂ አባወራነቱን ዘንግቶታል፣ሚስት ስያሜዋን እንጂ የባል ዘዉድነቷን ረስታዋለች… አፍቃሪ ነኝ ባይም ፍቅርን መጠቀሚያዉ እንጂ መኖሪያዉ ማረግ ከብዶታል… ወንድምም እንደ ወንድም እህትም እንደ እህት ሰዉም እንደ ሰዉ መሆን ከብዷቸዋል… መሆን ከከበዳቹ ወይ ስማችሁን አልያም ምግባራችሁን ቀይሩ መሆን ከብዶናል የያዝነዉ ስም ጥሎን ከብዶን ተሸንፈን መወዛወዝ መወዛወዝ ደርሶ መንገዳገድ ሆኖብናል መሰል ከስሙ ተጣብቀን ምግባሩን ረስተን ሰዉ መሆንን ፈርተን ከብዶናል ከብዶናል……. (እብዱ ነዉ ያለዉ እኔ አይደለሁም) ✍ይል @yilo15 @bravegenbyyil
Открыть канал и посмотреть медиа"የምትማረው ሰው ኹሉ እውቅና በሰጠው መንገድ ተጉዘህ ቦታና መተዳደርያ ለማግኘት ነው። የምታነበው ግን በሕይወት አንተ ብቻ እውቅና የሠጠኸው ደረጃ ላይ ለመድረስ ነው።" ደራሲ አለማየሁ ገላጋይ @yilo15 @bravegenbyyil
Открыть канал и посмотреть медиа#ማምሻ አንድ ተላምደናል፣በማህላችን ለንፋስ ማስገቢያ የሚከብድ ያህል መቀራረብን ተቀራርበናል፣ ነፍሶቻችን አንዱ ያለአንዱ አይኖር ይመስል መራራቅን ፈርተዋል፣ ታዲያ ካንቺ ወዲያ ላሉ ሰወች ነፍሴ ለማይገባቸዉ፤ስጋዬን ብቻ ለሚያዉቁት፣ ምንም ሳልጠበብ ቅንጣት ሳልጨነቅ እንደፈለኩ ሆኜ በነጻነት አዉርቼ ሁሉን ተናግሬ ሁሉን አስረድቼ፤ ነፍሴ የበላይነትን አግኝታ ትመለሳለች.. ግና አይኖቼ አንቺን ሲያዩ ወደኔ ስትቀርቢ እኔነቴ ተገፎ የሚሸሸኝ ይመስለኛል፣ አንደበቴ መኮላተፍ አይኖቼ መስለምለም ይጀምራሉ… ወደድኩሽ እንዳልል….. (የተንጠለጠለ ሀሳብ) ለምን ይሆን አንቺ ስትቀርቢኝ እኔነት ሚሸሸኝ ቃላቶቼ አጥረዉ ማዉራት የሚሳነኝ በሆነዉ ባልሆነዉ ብቻ ስታወሪ መሳቅ የሚቀለኝ ለምን ይሆን ዉዴ እሰቲ መልስ ስጪኝ ✍ ይል @yilo15 @bravegenbyyil
Открыть канал и посмотреть медиа🇪🇹 “ኢትዮጵያ ትነሳለች” 🇬🇭 የ “ጋና” የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ክዋሜ ንክሩማህ በአንድ ወቅት ስለ ኢትዮጵያ ግጥም ጽፈዋል!! “Ethiopia Shall Rise” by Kwame Nkrumah President Kwame Nkrumah, 🇬🇭🇪🇹 Ethiopia shall rise Ethiopia, Africa’s bright gem Set high among the verdant hills That gave birth to the unfailing Waters of the Nile Ethiopia shall rise Ethiopia, land of the wise; Ethiopia, bold cradle of Africa’s ancient rule And fertile school Of our African culture; Ethiopia, the wise Shall rise And remould with us the full figure Of Africa’s hopes And destiny. UniqueAfrica Great Africarica . #The_Real_One ❤ @bravegenbyyil
Открыть канал и посмотреть медиаየተጠለፉት የተሳፋሪ አውሮፕላኖች ከኒውዮርክ መንታ ህንፃዎች ጋር ተላትመው ሶስት ሺ ገደማ ሒወት የነጠቀበት የሴፕተምበር 9/11 የሽብር ጥቃት ድፍን 20 አመት ዛሬ ሞላው @atc_news @atc_news @atc_news @atc_news
Открыть канал и посмотреть медиаበዚህ ዓመት ሳንጣላ መታረቂያ ትንሽ ቦታ መጠለያ ትንሽ ብቻ መሰደጃ፡፡ ምንለበት ፤ ለምናልባት ብንተውለት !! ፍፁም መሆን ስለማንችል ትንሽ ባዶ እንዋዋል ፣ ከልባችን ደግ በኩል፡፡ ለአንጎላችን መላወሻ ትንሽ ቦታ እንተውለት " ምናልባት " የምንልበት፡፡ ልክ እንዳምና ፣ ለዚህ ዓመት ብንጣላ መታረቂያ ብንታሰር ይቅር ማያ ይቅር ብንል መታሰርያ ትንሽ እንተው ባዶ ቦታ፡፡ ጥግ ድረስ የለም ስራ ፣ ጥግ ድረስ የለም ፋታ፡፡ በልባችን ደግ በኩል ፣ እንፈልግ ባዶ ቦታ፡፡ የጳጉሜ ዓይነት ትንሽ ቦታ ለዘመን መለወጫ !! ((( ደግ ለሚያስቡ )))) //ነብይ መኮንን// አዲስ ባልነው ዓመት አሮጌ ያልነውን ትላንታችንን ሞሻሽረን ልናሳልፍ የምንተጋ ነን። በዚህ መሃል ከትዝታህ የጣልኩት መኖሩን እኔ እንጃ የማይሳሳብ፣ የማይወራረስ፣ የማይጠራራ ... ትናንት እና ዛሬ የለም። አዲሱ ዓመት እንኳን አዲስ የሆነው አጎጌው ኑሮለት አይደል። የኢትዮጵያ መልካም ዘመን በልጆቿ እጅ ላይ ነዉ፨ @yilo15 @bravegenbyyil
Открыть канал и посмотреть медиаSolo los usuarios registrados pueden compartir su opinión.
¡Sé el primero en compartir tu experiencia con este recurso!
CanalأثرOfrece contenido en árabe: publicaciones, cultura y noticias.
Flamable ChannelBeatsOfrece música de calidad para todos los gustos. Las pistas, mezclas y listas de reproducción están disponibles en línea en Telegram.
FireCalls- canal dinámico con🔥actualizaciones y actualizaciones para una notificación rápida.